የሐዋርያት ሥራ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 መከራ ከተቀበለ በኋላ ሕያው መሆኑን በብዙ አሳማኝ ማስረጃዎች አሳያቸው።+ እነሱም ለ40 ቀናት ያዩት ሲሆን እሱም ስለ አምላክ መንግሥት ይነግራቸው ነበር።+ የሐዋርያት ሥራ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እንደገና ተሰብስበው ሳሉ “ጌታ ሆይ፣ ለእስራኤል መንግሥትን መልሰህ የምታቋቁመው በዚህ ጊዜ ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+