የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/05 ገጽ 5
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 1/05 ገጽ 5

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር:- ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር ለማሰራጨት የሚደረግ ልዩ ዘመቻ። የካቲት:- ወደ ይሖዋ ቅረብ። መጋቢት:- ነቅተህ ጠብቅ! ሚያዝያ:- መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች።

◼ ከመጋቢት ወር ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “ማስተዋል በጎደለው ዓለም ውስጥ በጥበብ ተመላለሱ” የሚል ይሆናል።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ሐሙስ መጋቢት 24 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር የሚቻል ቢሆንም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ ሙሉ በሙሉ የምትጠልቅበትን ትክክለኛ ሰዓት ጠይቃችሁ ተረዱ። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን እንዲያከብር እናበረታታለን። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን ለማድረግ በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ ሁለት ወይም ሦስት ጉባኤዎች ካሉ አንዱ ወይም ሁለቱ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ መፈለግ ይችሉ ይሆናል። ሁሉም ከዝግጅቱ ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ፣ ከተቻለ ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ የ30 ደቂቃ ጊዜ እንድትመድቡ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። ተሳፋሪዎችን ማውረድንና መጫንን ጨምሮ ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታም ትኩረት መስጠት ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።

◼ በ2005 የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም የካቲት 14 የሚጀምር ሳምንት በሚቀርበው የተማሪ ክፍል ቁጥር 4 ላይ የጭብጥ ለውጥ ተደርጓል። በመሆኑም ይሄ ክፍል የተሰጣቸው ተማሪዎች ምርምር አድርገው ክፍላቸውን የሚያቀርቡት “ክርስቲያኖች ስለ ሂፕኖቲዝም ሊኖራቸው የሚገባው አመለካከት ምንድን ነው?” በሚለው ርዕስ ሳይሆን “ከአስማት ጋር ንክኪ ባላቸው ነገሮች መጠቀም ምን ጉዳት አለው?” በሚለው ጭብጥ ይሆናል።

◼ አዲስ የደረሱን:- ቻይንኛ:- T-21፣ T-26፤ ትግርኛ:- አምላክን አምልክ፤ ኡርዱ:- ነቅተህ ጠብቅ!

◼ በድጋሚ የደረሱን:- እንግሊዝኛ:- ጋይዳንስ፣ ጂሆቫስ ዊትነስስ፣ ላስቲንግ ፒስ ኤንድ ሃፒነስ፣ አወር ፕሮብሌምስ፣ ኮንኮርዳንስ፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (bi12)፣ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ 1986-2000፤ ትግርኛ:- የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ