ምሳሌ
14 ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትገነባለች፤+
ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች።
2 አካሄዱ ቅን የሆነ ሰው ይሖዋን ይፈራል፤
መንገዱ መሠሪ* የሆነ ግን ይንቀዋል።
3 በሞኝ ሰው አፍ የትዕቢት በትር አለ፤
የጥበበኞች ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።
4 ከብት በሌለበት ግርግሙ ንጹሕ ይሆናል፤
የበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ያስገኛል።
5 ሐቀኛ ምሥክር አይዋሽም፤
ሐሰተኛ ምሥክር ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል።+
6 ፌዘኛ ጥበብን ይፈልጋል፤ ሆኖም አያገኛትም፤
አስተዋይ ሰው ግን እውቀትን በቀላሉ ያገኛል።+
7 ከሞኝ ሰው ራቅ፤
ከከንፈሮቹ ምንም ዓይነት እውቀት አታገኝምና።+
10 ልብ የራሱን* ምሬት ያውቃል፤
ደስታውንም ሌላ ሰው ሊጋራው አይችልም።
11 የክፉዎች ቤት ይወድማል፤+
የቅኖች ድንኳን ግን ይበለጽጋል።
13 አንድ ሰው እየሳቀ እንኳ ልቡ ሊያዝን ይችላል፤
ደስታም በሐዘን ሊቋጭ ይችላል።
16 ጥበበኛ ሰው ጠንቃቃ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤
ሞኝ ግን ደንታ ቢስ ነው፤* ደግሞም ከልክ በላይ በራሱ ይመካል።
19 መጥፎ ሰዎች በጥሩ ሰዎች ፊት፣
ክፉዎችም በጻድቅ ደጃፍ ይሰግዳሉ።
21 ባልንጀራውን የሚንቅ ኃጢአት ይሆንበታል፤
ለችግረኞች የሚራራ ግን ደስተኛ ነው።+
22 ተንኮል የሚሸርቡ ሰዎች መንገድ ይስቱ የለም?
መልካም ነገር ለመሥራት የሚያስቡ ሰዎች ግን ታማኝ ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።+
23 በትጋት ያከናወኑት ነገር ሁሉ ጥቅም ያስገኛል፤
እንዲሁ ማውራት ግን ችግር ላይ ይጥላል።+
24 የጥበበኞች ዘውድ ሀብታቸው ነው፤
የሞኞች ቂልነት ግን ለከፋ ሞኝነት ይዳርጋል።+
25 እውነተኛ ምሥክር ሕይወትን* ይታደጋል፤
አታላይ ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል።
27 ይሖዋን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤
ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል።
28 የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ግርማ ነው፤+
ተገዢዎች የሌሉት ገዢ ግን ይጠፋል።
33 ጥበብ በአስተዋይ ልብ ውስጥ በጸጥታ ታርፋለች፤+
በሞኞች መካከል ግን ራሷን ትገልጣለች።
34 ጽድቅ አንድን ብሔር ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤+
ኃጢአት ግን ሕዝብን ታዋርዳለች።