ዘፍጥረት 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ። ዘፍጥረት 15:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚህ በኋላ የይሖዋ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጥቶ “አብራም አትፍራ።+ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ።+ የምታገኘውም ሽልማት እጅግ ታላቅ ይሆናል”+ አለው። ዘፍጥረት 15:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አብራምም በይሖዋ አመነ፤+ አምላክም ይህን ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት።+ ዘፍጥረት 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከእንግዲህ ስምህ አብራም* አይባልም፤ የብዙ ብሔር አባት ስለማደርግህ ስምህ አብርሃም* ይሆናል። ያዕቆብ 2:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ደግሞም “አብርሃም በይሖዋ* አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት”+ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እሱም የይሖዋ* ወዳጅ ለመባል በቃ።+