-
ዘሌዋውያን 14:49-53አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
49 ቤቱንም ከርኩሰት* ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ ይወስዳል።+ 50 አንደኛዋንም ወፍ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርዳታል። 51 ከዚያም የአርዘ ሊባኖስ እንጨቱን፣ ሂሶጱን፣ ደማቁን ቀይ ማግና በሕይወት ያለችውን ወፍ ወስዶ በታረደችው ወፍ ደምና ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፤ ወደ ቤቱም ሰባት ጊዜ ይርጨው።+ 52 ቤቱንም በወፏ ደም፣ ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ፣ በሕይወት ባለችው ወፍ፣ በአርዘ ሊባኖስ እንጨቱ፣ በሂሶጱና በደማቁ ቀይ ማግ ከርኩሰት* ያነጻዋል። 53 በሕይወት ያለችውንም ወፍ ከከተማዋ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቃታል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል።
-
-
ዘኁልቁ 19:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ካህኑም የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ሂሶጵና+ ደማቅ ቀይ ማግ ወስዶ ላሟ የምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምራል።
-