ዘፀአት 6:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 አሮን የነአሶን+ እህት የሆነችውን የአሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ። እሷም ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርን እና ኢታምርን ወለደችለት።+ ዘኁልቁ 4:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “የመብራቱን ዘይት፣+ ጥሩ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣+ ዘወትር የሚቀርበውን የእህል መባና የቅብዓት ዘይቱን+ የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር+ ነው። ቅዱሱን ስፍራና ዕቃዎቹን ጨምሮ የማደሪያ ድንኳኑን ሁሉና በውስጡ ያለውን ነገር በሙሉ የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የእሱ ነው።”
16 “የመብራቱን ዘይት፣+ ጥሩ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣+ ዘወትር የሚቀርበውን የእህል መባና የቅብዓት ዘይቱን+ የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር+ ነው። ቅዱሱን ስፍራና ዕቃዎቹን ጨምሮ የማደሪያ ድንኳኑን ሁሉና በውስጡ ያለውን ነገር በሙሉ የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የእሱ ነው።”