ዘዳግም 32:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ልዑሉ ለብሔራት ርስታቸውን ሲሰጥ፣+የአዳምን ልጆች* አንዱን ከሌላው ሲለያይ፣+በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክ+የሕዝቦችን ወሰን ደነገገ።+ ኢያሱ 24:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚያም ለይስሐቅ ያዕቆብንና ኤሳውን ሰጠሁት።+ በኋላም ለኤሳው ሴይር ተራራን ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤+ ያዕቆብና ልጆቹ ደግሞ ወደ ግብፅ ወረዱ።+ የሐዋርያት ሥራ 17:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም+ የሰውን ወገኖች በሙሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤+ የተወሰኑትን ዘመናትና የሰው ልጆች የሚኖሩበትንም ድንበር ደነገገ፤+