-
መሳፍንት 7:24, 25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ጌድዮንም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሁሉ “በምድያማውያን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያሉትን ውኃዎችና ዮርዳኖስን ያዙ” ብለው እንዲነግሯቸው መልእክተኞችን ላከ። በመሆኑም የኤፍሬም ሰዎች በሙሉ ተጠሩ፤ እነሱም እስከ ቤትባራ ድረስ ያሉትን ውኃዎችና ዮርዳኖስን ያዙ። 25 በተጨማሪም ሁለቱን የምድያም መኳንንት ማለትም ኦሬብን+ እና ዜብን ያዙ፤ ኦሬብን በኦሬብ ዓለት ላይ ገደሉት፤ ዜብን ደግሞ በዜብ የወይን መጭመቂያ ላይ ገደሉት። ምድያማውያንንም ማሳደዳቸውን ተያያዙት፤+ የኦሬብን እና የዜብን ጭንቅላት በዮርዳኖስ አካባቢ ወደነበረው ወደ ጌድዮን አመጡ።
-