ዘፍጥረት 5:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 እሱም “ይህ ልጅ፣ ይሖዋ በረገማት ምድር+ የተነሳ ከምንለፋው ልፋትና ከምንደክመው ድካም በማሳረፍ ያጽናናናል”* በማለት ስሙን ኖኅ*+ ብሎ ጠራው። ዘፍጥረት 41:51 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 51 ዮሴፍም “አምላክ የደረሰብኝን ችግር ሁሉና የአባቴን ቤት በሙሉ እንድረሳ አደረገኝ” በማለት ለበኩር ልጁ ምናሴ*+ የሚል ስም አወጣለት። ዘፀአት 2:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ከዚያ በኋላ ሙሴ ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ሰውየውም ልጁን ሲፓራን+ ለሙሴ ዳረለት። 22 እሷም ከጊዜ በኋላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም “በባዕድ አገር የምኖር የባዕድ አገር ሰው ሆንኩ”+ በማለት ስሙን ጌርሳም*+ አለው። ማቴዎስ 1:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እሱንም ኢየሱስ* ብለህ ትጠራዋለህ፤+ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና።”+
21 ከዚያ በኋላ ሙሴ ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ሰውየውም ልጁን ሲፓራን+ ለሙሴ ዳረለት። 22 እሷም ከጊዜ በኋላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም “በባዕድ አገር የምኖር የባዕድ አገር ሰው ሆንኩ”+ በማለት ስሙን ጌርሳም*+ አለው።