ዘፀአት 25:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ለእኔም መቅደስ ይሠሩልኛል፤ እኔም በመካከላቸው እኖራለሁ።*+ 1 ሳሙኤል 3:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የአምላክም መብራት+ ገና አልጠፋም፤ ሳሙኤልም የአምላክ ታቦት ባለበት የይሖዋ ቤተ መቅደስ*+ ውስጥ ተኝቶ ነበር። 2 ሳሙኤል 7:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ነቢዩ ናታንን+ “የእውነተኛው አምላክ ታቦት በድንኳን ውስጥ+ ተቀምጦ ሳለ ይኸው እኔ ከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ+ ቤት ውስጥ እየኖርኩ ነው” አለው።