25 ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ትሆናለህ፤+
እንከን የለሽ ለሆነ ሰው እንከን የለሽ ትሆናለህ፤+
26 ከንጹሕ ሰው ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤+
ጠማማ ለሆነ ሰው ግን ብልህ መሆንህን ታሳያለህ።+
27 ችግረኞችን ታድናለህና፤+
ትዕቢተኛውን ግን ታዋርዳለህ።+
28 ይሖዋ ሆይ፣ መብራቴን የምታበራው አንተ ነህና፤
አምላኬ ሆይ፣ ጨለማዬን ብርሃን የምታደርገው አንተ ነህ።+
29 በአንተ እርዳታ ወራሪውን ቡድን መጋፈጥ እችላለሁ፤+
በአምላክ ኃይል ቅጥር መውጣት እችላለሁ።+
30 የእውነተኛው አምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤+
የይሖዋ ቃል የነጠረ ነው።+
እሱ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።+