የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 24:14, 15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣+ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን*+ በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።+ 15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።

  • 1 ዜና መዋዕል 3:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 የኢዮዓቄም ወንዶች ልጆች ልጁ ኢኮንያን+ እና ልጁ ሴዴቅያስ ነበሩ።

  • 2 ዜና መዋዕል 36:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ከአሥር ቀን ገዛ፤ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 10 በዓመቱ መጀመሪያ* ላይ ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹን ልኮ በይሖዋ ቤት ካሉት ውድ ዕቃዎች+ ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው።+ የአባቱን ወንድም ሴዴቅያስንም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።+

  • ኤርምያስ 22:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ኮንያሁ የተባለው ይህ ሰው የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣

      ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነው?

      እሱም ሆነ ዘሮቹ ወደማያውቋት ምድር የተወረወሩትና

      የተጣሉት ለምንድን ነው?’+

  • ኤርምያስ 24:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው።+

  • ኤርምያስ 37:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 37 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የኢዮስያስን ልጅ ንጉሥ ሴዴቅያስን+ በይሁዳ ምድር ስላነገሠው በኢዮአቄም ልጅ በኮንያሁ*+ ፋንታ መግዛት ጀመረ።+

  • ኤርምያስ 52:31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ኤዊልሜሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን+ ፈታው፤* ከእስር ቤትም አወጣው፤+ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በ37ኛው ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በ25ኛው ቀን ነበር።

  • ማቴዎስ 1:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ኢዮስያስ+ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን በተጋዙበት ዘመን+ ኢኮንያንን+ እና ወንድሞቹን ወለደ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ