3 ንጉሡም ቆንጆ የሆኑትን ወጣት ደናግል ሁሉ ሰብስበው በሹሻን ግንብ ወደሚገኘው፣ ሴቶች ወደሚኖሩበት ቤት እንዲያመጧቸው በግዛቱ ውስጥ በሚገኙት አውራጃዎች ሁሉ+ ሰዎችን ይሹም። እነሱም የንጉሡ ጃንደረባና የሴቶቹ ጠባቂ በሆነው በሄጌ+ ኃላፊነት ሥር ይሁኑ፤ የውበት እንክብካቤም ይደረግላቸው። 4 ንጉሡ እጅግ ደስ የተሰኘባት ወጣትም በአስጢን ምትክ ንግሥት ትሆናለች።”+ ንጉሡም በሐሳቡ ደስ ተሰኘ፤ እንደተባለውም አደረገ።