የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 6:10-12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር+ ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣+ 11 አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ+ 12 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።+

  • ኢዮብ 31:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 ወርቅን መታመኛዬ አድርጌ፣

      ወይም ምርጥ የሆነውን ወርቅ ‘አንተ መመኪያዬ ነህ!’ ብዬ ከሆነ፣+

  • ኢዮብ 31:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ይህ በዳኞች ሊያስቀጣ የሚገባ በደል በሆነ ነበር፤

      በላይ ያለውን እውነተኛውን አምላክ መካድ ይሆንብኝ ነበርና።

  • ምሳሌ 11:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 በቁጣ ቀን ሀብት ፋይዳ አይኖረውም፤*+

      ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።+

  • ምሳሌ 11:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 በሀብቱ የሚታመን ሰው ይወድቃል፤+

      ጻድቅ ግን እንዳማረ ቅጠል ይለመልማል።+

  • ምሳሌ 23:4, 5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ሀብት ለማግኘት አትልፋ።+

      ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ።*

       5 ዓይንህን ስትጥልበት በዚያ አታገኘውም፤+

      የንስር ዓይነት ክንፎች አውጥቶ ወደ ሰማይ ይበርራልና።+

  • ማቴዎስ 6:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 “ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸውና ሌባ ገብቶ ሊሰርቀው በሚችልበት በምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ።*+

  • ማቴዎስ 6:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 “ለሁለት ጌቶች ባሪያ ሆኖ መገዛት የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል+ ወይም አንዱን ደግፎ ሌላውን ይንቃል። ለአምላክም ለሀብትም በአንድነት መገዛት አትችሉም።+

  • ማርቆስ 8:36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 ደግሞስ አንድ ሰው ዓለምን ሁሉ የራሱ ቢያደርግና ሕይወቱን* ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?+

  • ሉቃስ 12:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1 ጢሞቴዎስ 6:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 አሁን ባለው ሥርዓት* ሀብታም የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ እንዲሁም ተስፋቸውን አስተማማኝነት በሌለው ሀብት+ ላይ ሳይሆን የሚያስደስቱንን ነገሮች ሁሉ አትረፍርፎ በሚሰጠን አምላክ ላይ እንዲጥሉ እዘዛቸው።+

  • 1 ዮሐንስ 2:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ