መዝሙር 49:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ሆኖም አምላክ ከመቃብር* እጅ ይዋጀኛል፤*+እሱ ይይዘኛልና። (ሴላ) የሐዋርያት ሥራ 2:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 አምላክ ክርስቶስን በመቃብር* እንደማይተወውና ሥጋውም እንደማይበሰብስ* አስቀድሞ ተረድቶ ስለ ትንሣኤው ተናገረ።+ የሐዋርያት ሥራ 3:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በአንጻሩ ግን የሕይወትን “ዋና ወኪል”*+ ገደላችሁት። አምላክ ግን ከሞት አስነሳው፤ እኛም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን።+ ራእይ 1:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ባየሁት ጊዜ እንደሞተ ሰው ሆኜ እግሩ ሥር ወደቅኩ። እሱም ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፦ “አትፍራ። እኔ የመጀመሪያውና+ የመጨረሻው ነኝ፤+ 18 ሕያው የሆነውም እኔ ነኝ፤+ ሞቼም ነበር፤+ አሁን ግን ለዘላለም እኖራለሁ፤+ የሞትና የመቃብር* ቁልፎችም አሉኝ።+
17 ባየሁት ጊዜ እንደሞተ ሰው ሆኜ እግሩ ሥር ወደቅኩ። እሱም ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፦ “አትፍራ። እኔ የመጀመሪያውና+ የመጨረሻው ነኝ፤+ 18 ሕያው የሆነውም እኔ ነኝ፤+ ሞቼም ነበር፤+ አሁን ግን ለዘላለም እኖራለሁ፤+ የሞትና የመቃብር* ቁልፎችም አሉኝ።+