-
የሐዋርያት ሥራ 13:34-37አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
34 አምላክ ኢየሱስን የማይበሰብስ አካል ሰጥቶ ከሞት አስነስቶታል፤ ይህን አስቀድሞ በትንቢት ሲናገር ‘ለዳዊት ቃል የተገባውን የማይከስም * ታማኝ ፍቅር አሳያችኋለሁ’ ብሏል።+ 35 ስለዚህ በሌላም መዝሙር ላይ ‘ታማኝ አገልጋይህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ብሏል።+ 36 በአንድ በኩል፣ ዳዊት በሕይወት ዘመኑ አምላክን ካገለገለ* በኋላ በሞት አንቀላፍቷል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ መበስበስን አይቷል።+ 37 በሌላ በኩል ግን አምላክ ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ መበስበስን አላየም።+
-