-
1 ሳሙኤል 23:26-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
26 ከዚያም ሳኦል ከተራራው በአንደኛው በኩል ሲሆን ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ ከተራራው በሌላኛው በኩል ሆኑ። ዳዊት ከሳኦል ለማምለጥ እየተጣደፈ ነበር፤+ ይሁን እንጂ ሳኦልና አብረውት የነበሩት ሰዎች ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ተቃርበው ነበር።+ 27 ሆኖም አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ “ፍልስጤማውያን ምድሪቱን ስለወረሯት ቶሎ ድረስ!” አለው። 28 በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ+ ፍልስጤማውያንን ለመግጠም ሄደ። ያ ቦታ ‘የመለያያ ዓለት’ የተባለው በዚህ የተነሳ ነው።
-
-
2 ሳሙኤል 17:21, 22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ሰዎቹ ከሄዱም በኋላ አኪማዓስና ዮናታን ከጉድጓዱ ወጥተው ወደ ንጉሥ ዳዊት በመሄድ “እናንተ ሰዎች፣ ተነስታችሁ በፍጥነት ወንዙን ተሻገሩ፤ ምክንያቱም አኪጦፌል ስለ እናንተ እንዲህ እንዲህ የሚል ምክር ሰጥቷል” አሉት።+ 22 ዳዊትና አብሮት የነበረው ሕዝብ በሙሉ ወዲያውኑ ተነስተው ዮርዳኖስን ተሻገሩ። ጎህ ሲቀድም ዮርዳኖስን ሳይሻገር የቀረ አንድም ሰው አልነበረም።
-