ኢያሱ 2:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እንዲህም አለቻቸው፦ “ይሖዋ ምድሪቱን እንደሚሰጣችሁ አውቃለሁ፤+ እኛም እናንተን በመፍራት ተሸብረናል።+ የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ በእናንተ የተነሳ ልባቸው ከድቷቸዋል፤+ 10 ምክንያቱም ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ ይሖዋ ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀው+ እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ* በደመሰሳችኋቸው በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት፣ በሲሖንና+ በኦግ+ ላይ ምን እንዳደረጋችሁ ሰምተናል። ነህምያ 6:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ቅጥሩም በኤሉል* ወር በ25ኛው ቀን በ52 ቀናት ውስጥ ተሠርቶ ተጠናቀቀ። 16 ጠላቶቻችን በሙሉ ይህን ሲሰሙና በዙሪያችን ያሉት ብሔራትም ይህን ሲያዩ በኀፍረት ተዋጡ፤*+ ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን እርዳታ እንደሆነም ተገነዘቡ።
9 እንዲህም አለቻቸው፦ “ይሖዋ ምድሪቱን እንደሚሰጣችሁ አውቃለሁ፤+ እኛም እናንተን በመፍራት ተሸብረናል።+ የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ በእናንተ የተነሳ ልባቸው ከድቷቸዋል፤+ 10 ምክንያቱም ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ ይሖዋ ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀው+ እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ* በደመሰሳችኋቸው በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት፣ በሲሖንና+ በኦግ+ ላይ ምን እንዳደረጋችሁ ሰምተናል።
15 ቅጥሩም በኤሉል* ወር በ25ኛው ቀን በ52 ቀናት ውስጥ ተሠርቶ ተጠናቀቀ። 16 ጠላቶቻችን በሙሉ ይህን ሲሰሙና በዙሪያችን ያሉት ብሔራትም ይህን ሲያዩ በኀፍረት ተዋጡ፤*+ ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን እርዳታ እንደሆነም ተገነዘቡ።