3 የአምላክን ባሪያ የሙሴን መዝሙርና+ የበጉን+ መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፦
“ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣+ ሥራዎችህ ታላቅና አስደናቂ ናቸው።+ የዘላለም ንጉሥ ሆይ፣+ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።+ 4 ይሖዋ ሆይ፣ ለመሆኑ አንተን የማይፈራና ስምህን ከፍ ከፍ የማያደርግ ማን ነው? አንተ ብቻ ታማኝ ነህና!+ የጽድቅ ድንጋጌዎችህ ስለተገለጡ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”+