-
ዕብራውያን 10:5-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ስለዚህ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “‘መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ ከዚህ ይልቅ አካል አዘጋጀህልኝ። 6 ሙሉ በሙሉ በሚቃጠል መባና ለኃጢአት በሚቀርብ መባ ደስ አልተሰኘህም።’+ 7 በዚህ ጊዜ ‘እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ (ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል እንደተጻፈ) ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ’ አልኩ።”+ 8 በመጀመሪያ እንዲህ አለ፦ “መሥዋዕትን፣ መባን፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባንና ለኃጢአት የሚቀርብ መባን አልፈለግክም፤ እንዲሁም ደስ አልተሰኘህበትም።” እነዚህ መሥዋዕቶች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የሚቀርቡ ናቸው። 9 ከዚያም “እነሆ፣ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ።+ ሁለተኛውን ለማቋቋም የመጀመሪያውን ያስወግዳል።
-