2 ነገሥት 6:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የእውነተኛው አምላክ ሰው አገልጋይ በማለዳ ተነስቶ ወደ ውጭ ሲወጣ በፈረሶችና በጦር ሠረገሎች የተጠናከረ ሠራዊት ከተማዋን መክበቡን አየ። አገልጋዩም ወዲያውኑ “ወየው ጌታዬ! ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ። 16 ኤልሳዕ ግን “አይዞህ፣ አትፍራ!+ ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ”+ አለው። ኢሳይያስ 26:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሙሉ በሙሉ በአንተ የሚመኩትን* ትጠብቃለህ፤በአንተ ስለሚታመኑ+ዘላቂ ሰላም ትሰጣቸዋለህ።+ 2 ጴጥሮስ 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በመሆኑም ይሖዋ፣* ለአምላክ ያደሩ ሰዎችን ከፈተና እንዴት እንደሚያድንና+ ዓመፀኞችን ደግሞ በፍርድ ቀን ለሚደርስባቸው ጥፋት እንዴት ጠብቆ እንደሚያቆይ ያውቃል።+
15 የእውነተኛው አምላክ ሰው አገልጋይ በማለዳ ተነስቶ ወደ ውጭ ሲወጣ በፈረሶችና በጦር ሠረገሎች የተጠናከረ ሠራዊት ከተማዋን መክበቡን አየ። አገልጋዩም ወዲያውኑ “ወየው ጌታዬ! ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ። 16 ኤልሳዕ ግን “አይዞህ፣ አትፍራ!+ ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ”+ አለው።
9 በመሆኑም ይሖዋ፣* ለአምላክ ያደሩ ሰዎችን ከፈተና እንዴት እንደሚያድንና+ ዓመፀኞችን ደግሞ በፍርድ ቀን ለሚደርስባቸው ጥፋት እንዴት ጠብቆ እንደሚያቆይ ያውቃል።+