-
ሩት 1:16, 17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ከአንቺ እንድለይና ትቼሽ እንድመለስ አትማጸኚኝ፤ እኔ እንደሆነ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምታድሪበት አድራለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል።+ 17 በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በዚያም እቀበራለሁ። ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ቢኖር ይሖዋ አንዳች ነገር ያምጣብኝ፤ ከዚያም የከፋ ያድርግብኝ።”
-
-
1 ሳሙኤል 19:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 የሳኦል ልጅ ዮናታን ዳዊትን በጣም ይወደው+ ስለነበር ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “አባቴ ሳኦል ሊገድልህ ይፈልጋል። ስለዚህ እባክህ ጠዋት ላይ ተጠንቀቅ፤ ወደ አንድ ሰዋራ ቦታም ሄደህ ተሸሽገህ ቆይ።
-