የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 2:22-25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 በዚህ ጊዜ ኤሊ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ሆኖም ወንዶች ልጆቹ በሁሉም እስራኤላውያን ላይ ምን እንደሚያደርጉ+ እንዲሁም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደሚተኙ+ አንድም ሳይቀር ሰምቶ ነበር። 23 እሱም እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እንዲህ ያለ ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መጥፎ ነገር ሲናገሩ እሰማለሁ። 24 ልጆቼ፣ ትክክል አይደላችሁም፤ በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ሲናፈስ የምሰማው ወሬ ጥሩ አይደለም። 25 አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል ሌላ ሰው ይሖዋን ይለምንለት ይሆናል፤* ሆኖም አንድ ሰው ይሖዋን ቢበድል+ ማን ሊጸልይለት ይችላል?” እነሱ ግን የአባታቸውን ቃል ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ምክንያቱም ይሖዋ ሊገድላቸው ወስኖ ነበር።+

  • 1 ሳሙኤል 8:1-3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ውስጥ ፈራጆች ሆነው እንዲያገለግሉ ሾማቸው። 2 የበኩር ልጁ ስም ኢዩኤል ሲሆን የሁለተኛው ልጁ ስም ደግሞ አቢያህ+ ነበር፤ እነሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ። 3 ይሁንና ልጆቹ የእሱን ፈለግ አልተከተሉም፤ ከዚህ ይልቅ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም+ ለማግኘት ይጥሩ፣ ጉቦ ይቀበሉ+ እንዲሁም ፍርድ ያጣምሙ+ ነበር።

  • 2 ሳሙኤል 15:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ዳዊትም በኢየሩሳሌም አብረውት የነበሩትን አገልጋዮቹን በሙሉ ወዲያውኑ እንዲህ አላቸው፦ “ተነሱ፣ እንሽሽ፤+ አለዚያ አንዳችንም ከአቢሴሎም እጅ አናመልጥም! በፍጥነት መጥቶ እንዳይዘንና እንዳያጠፋን፣ ከተማዋንም በሰይፍ እንዳይመታ ቶሎ ብለን ከዚህ እንሂድ!”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ