13 በመጨረሻም ሳሙኤል ወደ ሳኦል ሲመጣ ሳኦል “ይሖዋ ይባርክህ። የይሖዋን ቃል ፈጽሜአለሁ” አለው። 14 ሳሙኤል ግን “ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎችና የከብቶች ድምፅ ምንድን ነው?” አለው።+ 15 በዚህ ጊዜ ሳኦል “ሕዝቡ ከአማሌቃውያን ላይ ወስዶ ያመጣቸው ናቸው፤ ከመንጋውና ከከብቶቹ መካከል ምርጥ የሆኑትን ለአምላክህ ለይሖዋ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳያጠፉ ተዉአቸው፤ የቀረውን ግን ሙሉ በሙሉ አጥፍተናል” አለው።