10 “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር+ ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣+ 11 አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ+ 12 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።+