የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 7:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን+ መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ+ ወሰድኩህ።

  • 2 ሳሙኤል 7:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ቤትህና መንግሥትህ ለዘላለም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል።”’”+

  • 2 ሳሙኤል 23:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 የእኔስ ቤት በአምላክ ፊት እንዲሁ አይደለም?

      እሱ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብቷልና፤+

      ቃል ኪዳኑም የተስተካከለና አስተማማኝ ነው።

      ምክንያቱም ይህ ለእኔ የተሟላ መዳንና ፍጹም ደስታ ነው፤

      ደግሞስ ቤቴ እንዲለመልም የሚያደርገው ለዚህ አይደለም?+

  • መዝሙር 89:28, 29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ታማኝ ፍቅሬን ለዘላለም አሳየዋለሁ፤+

      ከእሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።+

      29 ዘሩን ለዘላለም አጸናለሁ፤

      ዙፋኑም የሰማያትን ዕድሜ ያህል ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።+

  • ኤርምያስ 33:25, 26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማቋቋሜ+ እንዲሁም የሰማይንና የምድርን ሕግ* መደንገጌ የተረጋገጠ እንደሆነ ሁሉ፣+ 26 በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ልጆች* ላይ የሚነግሡ ገዢዎች ከዘሩ እንዳይታጡ የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር ፈጽሞ አልጥልም። ተማርከው የተወሰዱባቸውን መልሼ እሰበስባለሁና፤+ ርኅራኄም አሳያቸዋለሁ።’”+

  • የሐዋርያት ሥራ 13:34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 አምላክ ኢየሱስን የማይበሰብስ አካል ሰጥቶ ከሞት አስነስቶታል፤ ይህን አስቀድሞ በትንቢት ሲናገር ‘ለዳዊት ቃል የተገባውን የማይከስም * ታማኝ ፍቅር አሳያችኋለሁ’ ብሏል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ