-
ዘዳግም 30:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+ 2 እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ+ 3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+
-
-
ኢሳይያስ 66:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 የእስራኤል ልጆች በንጹሕ ዕቃ ስጦታ ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት እንደሚያመጡ፣ ወንድሞቻችሁን ሁሉ ለይሖዋ ስጦታ እንዲሆኑ ከየብሔራቱ በፈረሶች፣ በሠረገሎች፣ ጥላ ባላቸው ጋሪዎች፣ በበቅሎዎችና በፈጣን ግመሎች ጭነው ወደተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጧቸዋል”+ ይላል ይሖዋ።
-
-
ሕዝቅኤል 36:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ከብሔራት መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየአገሩም ሁሉ ሰብስቤ ወደ ምድራችሁ አመጣችኋለሁ።+
-