ኤርምያስ 16:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በመጀመሪያ፣ ለሠሩት በደልና ኃጢአት የሚገባቸውን ሙሉ ዋጋ እከፍላቸዋለሁ፤+ምድሬን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው በድን ምስሎች* አርክሰዋልና፤ርስቴንም አስነዋሪ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋል።’”+ ዳንኤል 9:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ሕግህን ተላልፈዋል፤ ቃልህን ባለመታዘዝም ለአንተ ጀርባቸውን ሰጥተዋል፤ በዚህም የተነሳ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ ሕግ የተጻፈውን እርግማንና መሐላ በእኛ ላይ አወረድክ፤+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና። 12 በእኛ ላይ ታላቅ ጥፋት በማምጣት በእኛ ላይና እኛን በገዙት ገዢዎቻችን ላይ* የተናገረውን ቃል ፈጸመብን፤+ በኢየሩሳሌም ላይ እንደተፈጸመው ያለ ነገር ከሰማይ በታች ታይቶ አያውቅም።+
18 በመጀመሪያ፣ ለሠሩት በደልና ኃጢአት የሚገባቸውን ሙሉ ዋጋ እከፍላቸዋለሁ፤+ምድሬን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው በድን ምስሎች* አርክሰዋልና፤ርስቴንም አስነዋሪ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋል።’”+
11 የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ሕግህን ተላልፈዋል፤ ቃልህን ባለመታዘዝም ለአንተ ጀርባቸውን ሰጥተዋል፤ በዚህም የተነሳ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ ሕግ የተጻፈውን እርግማንና መሐላ በእኛ ላይ አወረድክ፤+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና። 12 በእኛ ላይ ታላቅ ጥፋት በማምጣት በእኛ ላይና እኛን በገዙት ገዢዎቻችን ላይ* የተናገረውን ቃል ፈጸመብን፤+ በኢየሩሳሌም ላይ እንደተፈጸመው ያለ ነገር ከሰማይ በታች ታይቶ አያውቅም።+