መዝሙር 50:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ተግሣጼን* ትጠላለህና፤ለቃሌም ጀርባህን ትሰጣለህ።*+ ኢሳይያስ 42:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው? በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም? እነሱ በመንገዱ ለመሄድ አልፈለጉም፤ሕጉንም* አይታዘዙም።+ 25 ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓትበእስራኤል ላይ አፈሰሰ።+ የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም።+ አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም።+ ሕዝቅኤል 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የእስራኤል ቤት ግን ሊሰሙህ አይፈልጉም፤ እኔን መስማት አይፈልጉምና።+ የእስራኤል ቤት ወገኖች ሁሉ ግትርና ልበ ደንዳና ናቸው።+ ሶፎንያስ 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ማንንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ አልሆነችም፤+ ምንም ዓይነት ተግሣጽ አልተቀበለችም።+ በይሖዋ አልታመነችም፤+ ወደ አምላኳም አልቀረበችም።+
24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው? በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም? እነሱ በመንገዱ ለመሄድ አልፈለጉም፤ሕጉንም* አይታዘዙም።+ 25 ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓትበእስራኤል ላይ አፈሰሰ።+ የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም።+ አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም።+