ኤርምያስ 23:25, 26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “‘ሕልም አይቻለሁ! ሕልም አይቻለሁ!’+ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩ ነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ። 26 የሐሰት ትንቢት ይናገሩ ዘንድ ይህ ነገር በነቢያት ልብ ውስጥ የሚኖረው እስከ መቼ ነው? እነሱ ከገዛ ልባቸው ያመነጩትን ማታለያ የሚናገሩ ነቢያት ናቸው።+ ኤርምያስ 29:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚተነብዩላችሁ+ ስለ ቆላያህ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ ማአሴያህ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እሱም በፊታችሁ ይገድላቸዋል።
25 “‘ሕልም አይቻለሁ! ሕልም አይቻለሁ!’+ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩ ነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ። 26 የሐሰት ትንቢት ይናገሩ ዘንድ ይህ ነገር በነቢያት ልብ ውስጥ የሚኖረው እስከ መቼ ነው? እነሱ ከገዛ ልባቸው ያመነጩትን ማታለያ የሚናገሩ ነቢያት ናቸው።+
21 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚተነብዩላችሁ+ ስለ ቆላያህ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ ማአሴያህ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እሱም በፊታችሁ ይገድላቸዋል።