ማርቆስ 14:48, 49 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 48 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው?+ 49 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ እያስተማርኩ+ ከእናንተ ጋር ነበርኩ፤ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም። ይሁንና ይህ የሆነው ቅዱሳን መጻሕፍት እንዲፈጸሙ ነው።”+ ሉቃስ 22:52, 53 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 52 ከዚያም ኢየሱስ እሱን ለመያዝ የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደሱን ሹሞችና ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ መጣችሁ?+ 53 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ አብሬያችሁ ሳለሁ+ እኔን ለመያዝ እጃችሁን አላነሳችሁብኝም።+ ይሁንና ይህ የእናንተ ሰዓትና ጨለማ የሚነግሥበት ሰዓት ነው።”+
48 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው?+ 49 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ እያስተማርኩ+ ከእናንተ ጋር ነበርኩ፤ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም። ይሁንና ይህ የሆነው ቅዱሳን መጻሕፍት እንዲፈጸሙ ነው።”+
52 ከዚያም ኢየሱስ እሱን ለመያዝ የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደሱን ሹሞችና ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ መጣችሁ?+ 53 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ አብሬያችሁ ሳለሁ+ እኔን ለመያዝ እጃችሁን አላነሳችሁብኝም።+ ይሁንና ይህ የእናንተ ሰዓትና ጨለማ የሚነግሥበት ሰዓት ነው።”+