የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 4:1-10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፣ ዲያብሎስ+ ይፈትነው+ ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ መራው። 2 እሱም 40 ቀንና 40 ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። 3 ፈታኙም+ ቀርቦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች ዳቦ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። 4 እሱ ግን “‘ሰው ከይሖዋ* አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰ።+

      5 ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ+ ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት* ላይ አቁሞ+ 6 እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’”+ 7 ኢየሱስም “‘አምላክህን ይሖዋን* አትፈታተነው’ ተብሎም ተጽፏል” አለው።+

      8 እንደገናም ዲያብሎስ በጣም ረጅም ወደሆነ ተራራ ወስዶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉና ክብራቸውን አሳየው።+ 9 ከዚያም “አንድ ጊዜ ተደፍተህ ብታመልከኝ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው። 10 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “አንተ ሰይጣን፣ ከፊቴ ራቅ! ‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤+ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’+ ተብሎ ተጽፏልና” አለው።

  • ሉቃስ 4:1-13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ