-
ማቴዎስ 1:1-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
1 የዳዊት ልጅ፣+ የአብርሃም ልጅ+ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን* ታሪክ* የያዘ መጽሐፍ፦
2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤+
ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤+
ያዕቆብ ይሁዳንና+ ወንድሞቹን ወለደ፤
3 ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን+ ወለደ፤
ፋሬስ ኤስሮንን ወለደ፤+
ኤስሮን ራምን ወለደ፤+
4 ራም አሚናዳብን ወለደ፤
አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤+
ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤
5 ሰልሞን ከረዓብ+ ቦዔዝን ወለደ፤
ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤+
ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤+
6 እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።+
ዳዊት ከኦርዮ ሚስት ሰለሞንን ወለደ፤+
7 ሰለሞን ሮብዓምን ወለደ፤+
ሮብዓም አቢያህን ወለደ፤
አቢያህ አሳን ወለደ፤+
8 አሳ ኢዮሳፍጥን ወለደ፤+
ኢዮሳፍጥ ኢዮራምን ወለደ፤+
ኢዮራም ዖዝያን ወለደ፤
9 ዖዝያ ኢዮዓታምን ወለደ፤+
ኢዮዓታም አካዝን ወለደ፤+
አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤+
10 ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤+
ምናሴ አምዖንን ወለደ፤+
አምዖን ኢዮስያስን ወለደ፤+
11 ኢዮስያስ+ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን በተጋዙበት ዘመን+ ኢኮንያንን+ እና ወንድሞቹን ወለደ።
12 ወደ ባቢሎን ከተጋዙ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤
ሰላትያል ዘሩባቤልን ወለደ፤+
13 ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤
አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤
ኤልያቄም አዞርን ወለደ፤
14 አዞር ሳዶቅን ወለደ፤
ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤
አኪም ኤልዩድን ወለደ፤
15 ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤
አልዓዛር ማታንን ወለደ፤
ማታን ያዕቆብን ወለደ፤
16 ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደችው የማርያም ባል ነበር።+
17 ስለዚህ ጠቅላላው ትውልድ፣ ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ፣ ከዳዊት አንስቶ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን እስከተጋዙበት ጊዜ ድረስ 14 ትውልድ እንዲሁም ወደ ባቢሎን ከተጋዙበት ዘመን እስከ ክርስቶስ ድረስ 14 ትውልድ ነው።
-