2 ቆሮንቶስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ይሖዋ* መንፈስ ነው፤+ የይሖዋ* መንፈስ ባለበት ደግሞ ነፃነት አለ።+ 1 ጢሞቴዎስ 1:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እንግዲህ ለማይጠፋውና+ ለማይታየው፣+ እሱ ብቻ አምላክ ለሆነው+ ለዘላለሙ ንጉሥ+ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን። አሜን። ዕብራውያን 11:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ደግሞም በእምነት ግብፅን ለቆ ወጣ፤+ ሆኖም ይህን ያደረገው የንጉሡን ቁጣ ፈርቶ አይደለም፤+ የማይታየውን አምላክ+ እንደሚያየው አድርጎ በጽናት ቀጥሏልና።