ምሳሌ 10:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ንጹሕ አቋሙን* ጠብቆ የሚሄድ ያለስጋት ይመላለሳል፤+መንገዱን ጠማማ የሚያደርግ ግን ይጋለጣል።+ 2 ቆሮንቶስ 10:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ተቀባይነት የሚያገኘው ራሱን ብቁ እንደሆነ አድርጎ የሚያቀርብ ሳይሆን+ ይሖዋ* ብቁ ነው የሚለው ሰው ነውና።+ 1 ጢሞቴዎስ 5:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በይፋ የታወቀ ስለሚሆን ወዲያውኑ ፍርድ ያስከትላል፤ የሌሎቹ ሰዎች ኃጢአት ደግሞ ውሎ አድሮ መታወቁ አይቀርም።+ 25 በተመሳሳይም መልካም ሥራዎች በይፋ የታወቁ ናቸው፤+ በይፋ ያልታወቁትም ቢሆኑ ተደብቀው ሊቀሩ አይችሉም።+
24 የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በይፋ የታወቀ ስለሚሆን ወዲያውኑ ፍርድ ያስከትላል፤ የሌሎቹ ሰዎች ኃጢአት ደግሞ ውሎ አድሮ መታወቁ አይቀርም።+ 25 በተመሳሳይም መልካም ሥራዎች በይፋ የታወቁ ናቸው፤+ በይፋ ያልታወቁትም ቢሆኑ ተደብቀው ሊቀሩ አይችሉም።+