-
1 ጢሞቴዎስ 6:3-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 አንድ ሰው የተለየ ትምህርት ቢያስተምርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካስተማረው ትክክለኛ* ትምህርትም+ ሆነ ለአምላክ ማደርን ከሚያበረታታው ትምህርት+ ጋር የማይስማማ ቢሆን 4 ይህ ሰው በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያስተውል ነው።+ ስለ ቃላት የመጨቃጨቅና የመከራከር አባዜ* የተጠናወተው ነው።+ እንዲህ ያሉ ነገሮች ቅናት፣ ጠብ፣ ስም ማጥፋትና* መጥፎ ጥርጣሬ ያስከትላሉ፤ 5 በተጨማሪም ለአምላክ ማደር ጥቅም ማግኛ እንደሆነ አድርገው በሚያስቡ፣+ አእምሯቸው በተበላሸና+ እውነትን መረዳት ባቆሙ ሰዎች መካከል ተራ በሆኑ ጉዳዮች የማያባራ ጭቅጭቅ ያስነሳሉ።
-
-
2 ጴጥሮስ 3:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ ሕግ የሚተላለፉ ሰዎች በሚፈጽሙት ስህተት ከእነሱ ጋር ተታልላችሁ እንዳትወሰዱና ጽኑ አቋማችሁ እንዳይናጋ ተጠንቀቁ።+
-