9 ደግሞም ሕግ የሚወጣው ለጻድቅ ሰው ሳይሆን ሕግ ለሚተላለፉና+ ለዓመፀኞች፣ ፈሪሃ አምላክ ለሌላቸውና ለኃጢአተኞች፣ ታማኞች ላልሆኑና ቅዱስ የሆነውን ለሚንቁ፣ አባትንና እናትን ለሚገድሉ እንዲሁም ለነፍሰ ገዳዮች መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል፤ 10 በተጨማሪም ለሴሰኞች፣ ግብረ ሰዶም ለሚፈጽሙ ወንዶች፣ ለአፋኞች፣ ለውሸታሞችና በሐሰት ለሚምሉ እንዲሁም ትክክለኛውን ትምህርት+ ለሚጻረሩ ነገሮች ሁሉ ነው፤