የሐዋርያት ሥራ 20:29, 30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 እኔ ከሄድኩ በኋላ ጨካኝ* ተኩላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡና+ መንጋውን በርኅራኄ እንደማይዙ አውቃለሁ፤ 30 ከእናንተ መካከል እንኳ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሳቸው ለመሳብ ጠማማ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ይነሳሉ።+ 1 ጢሞቴዎስ 4:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ይሁን እንጂ በመንፈስ መሪነት የተነገረው ቃል በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች ከመናፍስት ለሚመነጩ አሳሳች ቃሎችና*+ ለአጋንንት ትምህርቶች ጆሯቸውን በመስጠት ከእምነት መውጣታቸው እንደማይቀር በግልጽ ይናገራል፤ 2 ጴጥሮስ 2:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሁን እንጂ በሕዝቡ መካከል ሐሰተኛ ነቢያት እንደነበሩ ሁሉ በእናንተም መካከል ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይነሳሉ።+ እነዚህ ሰዎች ጥፋት የሚያስከትል ኑፋቄ በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውን+ ጌታ እንኳ ሳይቀር ክደው በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋት ያመጣሉ። 2 ጴጥሮስ 3:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይህም ቀደም ሲል ቅዱሳን ነቢያት የተናገሩትን ቃል* እንዲሁም ጌታችንና አዳኛችን በሐዋርያት* አማካኝነት የሰጠውን ትእዛዝ እንድታስታውሱ ለመርዳት ነው። 3 ከሁሉ አስቀድሞ ይህን እወቁ፦ በመጨረሻዎቹ ቀናት የራሳቸውን ምኞት እየተከተሉ የሚያፌዙ ፌዘኞች ይመጣሉ።+
29 እኔ ከሄድኩ በኋላ ጨካኝ* ተኩላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡና+ መንጋውን በርኅራኄ እንደማይዙ አውቃለሁ፤ 30 ከእናንተ መካከል እንኳ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሳቸው ለመሳብ ጠማማ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ይነሳሉ።+
4 ይሁን እንጂ በመንፈስ መሪነት የተነገረው ቃል በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች ከመናፍስት ለሚመነጩ አሳሳች ቃሎችና*+ ለአጋንንት ትምህርቶች ጆሯቸውን በመስጠት ከእምነት መውጣታቸው እንደማይቀር በግልጽ ይናገራል፤
2 ይሁን እንጂ በሕዝቡ መካከል ሐሰተኛ ነቢያት እንደነበሩ ሁሉ በእናንተም መካከል ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይነሳሉ።+ እነዚህ ሰዎች ጥፋት የሚያስከትል ኑፋቄ በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውን+ ጌታ እንኳ ሳይቀር ክደው በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋት ያመጣሉ።
2 ይህም ቀደም ሲል ቅዱሳን ነቢያት የተናገሩትን ቃል* እንዲሁም ጌታችንና አዳኛችን በሐዋርያት* አማካኝነት የሰጠውን ትእዛዝ እንድታስታውሱ ለመርዳት ነው። 3 ከሁሉ አስቀድሞ ይህን እወቁ፦ በመጨረሻዎቹ ቀናት የራሳቸውን ምኞት እየተከተሉ የሚያፌዙ ፌዘኞች ይመጣሉ።+