የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 50
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • በባቢሎን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-46)

        • ከባቢሎን ሽሹ (8)

        • እስራኤል ወደ ምድሩ ይመለሳል (17-19)

        • የባቢሎን ውኃ ይደርቃል (38)

        • ባቢሎን የሚኖርባት አይገኝም (39, 40)

ኤርምያስ 50:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:1

ኤርምያስ 50:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:8፤ ራእይ 14:8
  • +ኢሳ 46:1፤ ኤር 51:44

ኤርምያስ 50:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:17፤ ኤር 51:11, 48

ኤርምያስ 50:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:12፤ ኤር 3:18፤ ሆሴዕ 1:11
  • +ኤር 31:8, 9
  • +ሆሴዕ 3:5

ኤርምያስ 50:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 35:10
  • +ኤር 31:31

ኤርምያስ 50:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 53:6
  • +ኤር 10:21፤ 23:2፤ ሕዝ 34:2, 6

ኤርምያስ 50:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 79:6, 7

ኤርምያስ 50:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አውራ በጎችና አውራ ፍየሎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 48:20፤ ኤር 51:6, 45፤ ዘካ 2:7፤ 2ቆሮ 6:17፤ ራእይ 18:2, 4

ኤርምያስ 50:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 21:2፤ ኤር 51:11, 27, 28, 48፤ ዳን 5:28, 30
  • +ኢሳ 13:17, 18

ኤርምያስ 50:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:12፤ 27:6, 7
  • +ራእይ 17:16

ኤርምያስ 50:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 1:21
  • +ኢሳ 14:4-6፤ 47:6፤ ኤር 30:16

ኤርምያስ 50:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 47:8
  • +ኢሳ 13:20, 21

ኤርምያስ 50:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 1:15
  • +ኤር 25:12
  • +ኤር 51:37

ኤርምያስ 50:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የምትረግጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:35, 36
  • +ኢሳ 13:18፤ ኤር 51:11

ኤርምያስ 50:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:58
  • +ኤር 51:6, 11
  • +መዝ 137:8፤ ራእይ 18:6

ኤርምያስ 50:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:23
  • +ኢሳ 13:14፤ ኤር 51:9

ኤርምያስ 50:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 23:1፤ 50:6፤ ሕዝ 34:5
  • +ኤር 2:15
  • +2ነገ 17:6፤ ኢሳ 8:7
  • +2ነገ 25:1፤ 2ዜና 36:17፤ ኤር 4:7

ኤርምያስ 50:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:35፤ ኢሳ 14:25፤ ሶፎ 2:13

ኤርምያስ 50:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱ እስክትጠግብ ድረስ ትመገባለች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:16፤ 65:10፤ ኤር 23:3፤ 33:7፤ ሕዝ 34:14፤ ሚክ 2:12
  • +ሚክ 7:14
  • +ኤር 31:6
  • +አብ 19

ኤርምያስ 50:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 44:22፤ ኤር 31:34፤ ሚክ 7:19

ኤርምያስ 50:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለጥፋት ለያቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 23:22, 23

ኤርምያስ 50:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 14:5, 6፤ ኤር 51:20
  • +ኤር 51:41፤ ራእይ 18:15, 16

ኤርምያስ 50:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:31፤ ዳን 5:30፤ ራእይ 18:8

ኤርምያስ 50:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:5፤ ኤር 51:11

ኤርምያስ 50:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:27
  • +ኤር 50:10
  • +ኢሳ 14:22, 23

ኤርምያስ 50:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 34:6, 7፤ ሕዝ 39:18

ኤርምያስ 50:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 94:1፤ ኤር 51:11

ኤርምያስ 50:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሚረግጡትንም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 50:14
  • +መዝ 137:8፤ ኤር 51:56
  • +ሰቆ 3:64፤ ራእይ 18:6
  • +ኢሳ 14:13

ኤርምያስ 50:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ጸጥ ይላሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:17, 18

ኤርምያስ 50:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 14:13፤ ዳን 4:30
  • +ኤር 51:25

ኤርምያስ 50:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:26

ኤርምያስ 50:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 47:6
  • +ኢሳ 14:17

ኤርምያስ 50:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:14፤ ራእይ 18:8
  • +ኢሳ 47:4
  • +ኢሳ 14:3, 4
  • +ኤር 51:24
  • +ሰቆ 3:59

ኤርምያስ 50:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 47:13፤ ኤር 51:57፤ ዳን 5:7

ኤርምያስ 50:36

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሐሰተኛ ነቢያት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:30

ኤርምያስ 50:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:8
  • +ኢሳ 45:3

ኤርምያስ 50:38

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 44:27፤ ኤር 51:36, 37፤ ራእይ 16:12
  • +ኢሳ 46:1፤ ኤር 51:44, 52፤ ዳን 5:1, 4

ኤርምያስ 50:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:20, 21፤ ኤር 51:37፤ ራእይ 18:2
  • +ኤር 25:12፤ 51:43, 64

ኤርምያስ 50:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:19
  • +ዘፍ 19:24, 25፤ ይሁዳ 7
  • +ኤር 51:26

ኤርምያስ 50:41

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 45:1፤ ኤር 51:11, 27, 28
  • +ኢሳ 13:5, 17

ኤርምያስ 50:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 50:9
  • +መዝ 137:8፤ ኢሳ 13:17, 18
  • +ኤር 51:42
  • +ኤር 51:27

ኤርምያስ 50:43

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:31
  • +ዳን 5:6

ኤርምያስ 50:44

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:25
  • +ኤር 49:19-21

ኤርምያስ 50:45

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የመከረውን ምክርና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:11
  • +ኢሳ 13:1, 20፤ ኤር 51:43

ኤርምያስ 50:46

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 18:9

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 50:1ኢሳ 13:1
ኤር. 50:2ኤር 51:8፤ ራእይ 14:8
ኤር. 50:2ኢሳ 46:1፤ ኤር 51:44
ኤር. 50:3ኢሳ 13:17፤ ኤር 51:11, 48
ኤር. 50:4ኢሳ 11:12፤ ኤር 3:18፤ ሆሴዕ 1:11
ኤር. 50:4ኤር 31:8, 9
ኤር. 50:4ሆሴዕ 3:5
ኤር. 50:5ኢሳ 35:10
ኤር. 50:5ኤር 31:31
ኤር. 50:6ኢሳ 53:6
ኤር. 50:6ኤር 10:21፤ 23:2፤ ሕዝ 34:2, 6
ኤር. 50:7መዝ 79:6, 7
ኤር. 50:8ኢሳ 48:20፤ ኤር 51:6, 45፤ ዘካ 2:7፤ 2ቆሮ 6:17፤ ራእይ 18:2, 4
ኤር. 50:9ኢሳ 21:2፤ ኤር 51:11, 27, 28, 48፤ ዳን 5:28, 30
ኤር. 50:9ኢሳ 13:17, 18
ኤር. 50:10ኤር 25:12፤ 27:6, 7
ኤር. 50:10ራእይ 17:16
ኤር. 50:11ሰቆ 1:21
ኤር. 50:11ኢሳ 14:4-6፤ 47:6፤ ኤር 30:16
ኤር. 50:12ኢሳ 47:8
ኤር. 50:12ኢሳ 13:20, 21
ኤር. 50:13ዘካ 1:15
ኤር. 50:13ኤር 25:12
ኤር. 50:13ኤር 51:37
ኤር. 50:14ኤር 51:35, 36
ኤር. 50:14ኢሳ 13:18፤ ኤር 51:11
ኤር. 50:15ኤር 51:58
ኤር. 50:15ኤር 51:6, 11
ኤር. 50:15መዝ 137:8፤ ራእይ 18:6
ኤር. 50:16ኤር 51:23
ኤር. 50:16ኢሳ 13:14፤ ኤር 51:9
ኤር. 50:17ኤር 23:1፤ 50:6፤ ሕዝ 34:5
ኤር. 50:17ኤር 2:15
ኤር. 50:172ነገ 17:6፤ ኢሳ 8:7
ኤር. 50:172ነገ 25:1፤ 2ዜና 36:17፤ ኤር 4:7
ኤር. 50:182ነገ 19:35፤ ኢሳ 14:25፤ ሶፎ 2:13
ኤር. 50:19ኢሳ 11:16፤ 65:10፤ ኤር 23:3፤ 33:7፤ ሕዝ 34:14፤ ሚክ 2:12
ኤር. 50:19ሚክ 7:14
ኤር. 50:19ኤር 31:6
ኤር. 50:19አብ 19
ኤር. 50:20ኢሳ 44:22፤ ኤር 31:34፤ ሚክ 7:19
ኤር. 50:21ሕዝ 23:22, 23
ኤር. 50:23ኢሳ 14:5, 6፤ ኤር 51:20
ኤር. 50:23ኤር 51:41፤ ራእይ 18:15, 16
ኤር. 50:24ኤር 51:31፤ ዳን 5:30፤ ራእይ 18:8
ኤር. 50:25ኢሳ 13:5፤ ኤር 51:11
ኤር. 50:26ኤር 51:27
ኤር. 50:26ኤር 50:10
ኤር. 50:26ኢሳ 14:22, 23
ኤር. 50:27ኢሳ 34:6, 7፤ ሕዝ 39:18
ኤር. 50:28መዝ 94:1፤ ኤር 51:11
ኤር. 50:29ኤር 50:14
ኤር. 50:29መዝ 137:8፤ ኤር 51:56
ኤር. 50:29ሰቆ 3:64፤ ራእይ 18:6
ኤር. 50:29ኢሳ 14:13
ኤር. 50:30ኢሳ 13:17, 18
ኤር. 50:31ኢሳ 14:13፤ ዳን 4:30
ኤር. 50:31ኤር 51:25
ኤር. 50:32ኤር 51:26
ኤር. 50:33ኢሳ 47:6
ኤር. 50:33ኢሳ 14:17
ኤር. 50:34ኢሳ 41:14፤ ራእይ 18:8
ኤር. 50:34ኢሳ 47:4
ኤር. 50:34ኢሳ 14:3, 4
ኤር. 50:34ኤር 51:24
ኤር. 50:34ሰቆ 3:59
ኤር. 50:35ኢሳ 47:13፤ ኤር 51:57፤ ዳን 5:7
ኤር. 50:36ኤር 51:30
ኤር. 50:37ኢሳ 13:8
ኤር. 50:37ኢሳ 45:3
ኤር. 50:38ኢሳ 44:27፤ ኤር 51:36, 37፤ ራእይ 16:12
ኤር. 50:38ኢሳ 46:1፤ ኤር 51:44, 52፤ ዳን 5:1, 4
ኤር. 50:39ኢሳ 13:20, 21፤ ኤር 51:37፤ ራእይ 18:2
ኤር. 50:39ኤር 25:12፤ 51:43, 64
ኤር. 50:40ኢሳ 13:19
ኤር. 50:40ዘፍ 19:24, 25፤ ይሁዳ 7
ኤር. 50:40ኤር 51:26
ኤር. 50:41ኢሳ 45:1፤ ኤር 51:11, 27, 28
ኤር. 50:41ኢሳ 13:5, 17
ኤር. 50:42ኤር 50:9
ኤር. 50:42መዝ 137:8፤ ኢሳ 13:17, 18
ኤር. 50:42ኤር 51:42
ኤር. 50:42ኤር 51:27
ኤር. 50:43ኤር 51:31
ኤር. 50:43ዳን 5:6
ኤር. 50:44ኢሳ 41:25
ኤር. 50:44ኤር 49:19-21
ኤር. 50:45ኤር 51:11
ኤር. 50:45ኢሳ 13:1, 20፤ ኤር 51:43
ኤር. 50:46ራእይ 18:9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 50:1-46

ኤርምያስ

50 ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ባቢሎን+ ይኸውም ስለ ከለዳውያን ምድር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦

 2 “በብሔራት መካከል ይህን ተናገሩ፤ ደግሞም አውጁ።

ምልክት* አቁሙ፤ ይህን አውጁ።

ምንም ነገር አትደብቁ!

እንዲህም በሉ፦ ‘ባቢሎን ተይዛለች።+

ቤል ኀፍረት ተከናንቧል።+

ሜሮዳክ በፍርሃት ርዷል።

ምስሎቿ ተዋርደዋል።

አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቿ* ተሸብረዋል።’

 3 ከሰሜን አንድ ብሔር በእሷ ላይ ተነስቷልና።+

እሱም ምድሪቷን አስፈሪ ቦታ ያደርጋታል፤

በእሷ ውስጥ የሚኖር ሰው የለም።

ሰውም ሆነ እንስሳ ሸሽቷል፤

አካባቢውን ለቀው ሄደዋል።”

4 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የእስራኤል ሕዝብም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ይመጣሉ።+ እያለቀሱ ይሄዳሉ፤+ በአንድነትም አምላካቸውን ይሖዋን ይፈልጋሉ።+ 5 ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤+ ፊታቸውንም ወደዚያ አቅጣጫ አዙረው ‘ኑ፣ ከይሖዋ ጋር የማይረሳ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንግባ’ ይላሉ።+ 6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች መንጋ ሆኗል።+ የገዛ እረኞቻቸው እንዲባዝኑ አድርገዋቸዋል።+ ወደ ተራሮች ነዷቸው፤ እነሱም በየተራራውና በየኮረብታው ተቅበዘበዙ። ማረፊያ ቦታቸውን ረሱ። 7 ያገኟቸውም ሁሉ ዋጧቸው፤+ ጠላቶቻቸውም ‘በይሖዋ ይኸውም የጽድቅ መኖሪያና የአባቶቻቸው ተስፋ በሆነው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ እኛ በደለኞች አይደለንም’ ብለዋል።”

 8 “ከባቢሎን መካከል ወጥታችሁ ሽሹ፤

ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፤+

መንጋውንም እንደሚመሩ እንስሳት* ሁኑ።

 9 እነሆ፣ እኔ ከሰሜን ምድር የታላላቅ ብሔራትን ጉባኤ አስነስቼ

በባቢሎን ላይ አመጣባታለሁና።+

እነሱም እሷን ለመውጋት ይሰለፋሉ፤

በዚያም በኩል ትያዛለች።

ፍላጻዎቻቸው እንደ ተዋጊ ፍላጻዎች ናቸው፤

ወላጆችን የወላድ መሃን ያደርጋሉ፤+

ዓላማቸውን ሳይፈጽሙ አይመለሱም።

10 የከለዳውያን ምድር ትበዘበዛለች።+

የሚበዘብዟትም ሁሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይመዘብሯታል”+ ይላል ይሖዋ።

11 “እናንተ እጅግ ደስ ብሏችኋልና፤+

የገዛ ርስቴን ስትመዘብሩ ሐሴት አድርጋችኋል።+

በለምለም ሣር ላይ እንዳለች ጊደር ፈንጭታችኋልና፤

እንደ ድንጉላ ፈረሶችም አሽካክታችኋል።

12 እናታችሁ ለኀፍረት ተዳርጋለች።+

የወለደቻችሁም እጅግ አዝናለች።

እነሆ፣ ከብሔራት ሁሉ ያነሰች፣

ውኃ የሌለባት ምድረ በዳና በረሃ ሆናለች።+

13 ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ሰው የማይኖርባት ምድር ትሆናለች፤+

ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናለች።+

በባቢሎን በኩል የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታታል፤

ከደረሱባትም መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳ ያፏጫል።+

14 እናንተ ደጋን የምትወጥሩ* ሁሉ፣

ባቢሎንን ለመውጋት በዙሪያዋ ተሰለፉ።

ፍላጻ ወርውሩባት፤ በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራች+

አንድም ፍላጻ አታስቀሩ።+

15 በዙሪያዋ ሁሉ ቀረርቶ አሰሙ።

እጇን ሰጥታለች።

ዓምዶቿ ወድቀዋል፤ ቅጥሮቿ ፈርሰዋል፤+

ይህ የይሖዋ በቀል ነውና።+

እሷን ተበቀሏት።

እንዳደረገችው አድርጉባት።+

16 ዘር የሚዘራውንና

በመከር ወቅት ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አስወግዱ።+

ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለሳል፤

እያንዳንዱም ወደ ገዛ ምድሩ ይሸሻል።+

17 “የእስራኤል ሕዝብ የባዘነ በግ ነው።+ እንዲባዝን ያደረጉት አንበሶች ናቸው።+ በመጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤+ ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* አጥንቱን ቆረጣጠመው።+ 18 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በአሦር ንጉሥ ላይ እንዳደረግኩት ሁሉ በባቢሎን ንጉሥና በምድሩ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 19 እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤+ እሱም በቀርሜሎስና በባሳን ይሰማራል፤+ በኤፍሬምና+ በጊልያድ+ ተራሮችም ላይ እስኪጠግብ ድረስ ይመገባል።’”*

20 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣

“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤

ሆኖም አይገኝም፤

የይሁዳም ኃጢአት አይገኝም፤

እንዲተርፉ ያደረግኳቸውን ይቅር እላቸዋለሁና።”+

21 “በመረታይም ምድር ላይ ውጣ፤ በጰቆድ+ ነዋሪዎችም ላይ ተነሳ።

ነዋሪዎቹ ይጨፍጨፉ፤ ሙሉ በሙሉም ይጥፉ”* ይላል ይሖዋ።

“ያዘዝኩህንም ሁሉ አድርግ።

22 በምድሪቱ ላይ የጦርነትና

የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል።

23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ተቆረጠ! እንዴትስ ተሰበረ!+

ባቢሎን በብሔራት መካከል እንዴት መቀጣጫ ሆነች!+

24 ባቢሎን ሆይ፣ በአንቺ ላይ ወጥመድ ዘርግቻለሁ፤ ደግሞም ተይዘሻል፤

አንቺ ግን አልታወቀሽም።

ተገኘሽ፤ እንዲሁም ተያዝሽ፤+

የተቃወምሽው ይሖዋን ነውና።

25 ይሖዋ ግምጃ ቤቱን ከፍቷል፤

የቁጣ የጦር መሣሪያዎቹንም ያወጣል።+

ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ

በከለዳውያን ምድር የሚሠራው ሥራ አለና።

26 ከሩቅ ቦታ መጥታችሁ በእሷ ላይ ውጡ።+

ጎተራዎቿን ክፈቱ።+

እንደ እህል ክምር ከምሯት።

ፈጽማችሁ አጥፏት።+

አንድም ሰው አታስቀሩላት።

27 ወይፈኖቿን ሁሉ እረዱ፤+

ወደ እርድ ቦታ ይውረዱ።

ቀናቸው ይኸውም የሚመረመሩበት ጊዜ

ስለደረሰ ወዮላቸው!

28 የአምላካችንን የይሖዋን በቀል፣

ስለ ቤተ መቅደሱ ሲል የወሰደውን የበቀል እርምጃ+ በጽዮን ለማወጅ

ከባቢሎን ምድር የሚሸሹና

አምልጠው የሚሄዱ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።

29 ቀስተኞችን፣ ደጋን የሚወጥሩትንም* ሁሉ

በባቢሎን ላይ ጥሩ።+

በዙሪያዋም ስፈሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ።

እንደ ሥራዋ መልሱላት።+

እሷ እንዳደረገችው ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉባት።+

በይሖዋ ላይ ይኸውም በእስራኤል ቅዱስ ላይ

የእብሪት ድርጊት ፈጽማለችና።+

30 በመሆኑም ወጣቶቿ በአደባባዮቿ ይወድቃሉ፤+

በዚያም ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይጠፋሉ”* ይላል ይሖዋ።

31 “አንቺ ዓመፀኛ፣+ እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤

“ቀንሽ ይኸውም አንቺን ተጠያቂ የማደርግበት ጊዜ ይመጣልና።

32 አንቺ ዓመፀኛ ተሰናክለሽ ትወድቂያለሽ፤

የሚያነሳሽም አይኖርም።+

ከተሞችሽንም በእሳት አነዳለሁ፤

በዙሪያሽም ያለውን ሁሉ ይበላል።”

33 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቁነዋል፤

ማርከው የወሰዷቸውም ሁሉ ጠፍረው ይዘዋቸዋል።+

እነሱን ለመልቀቅ ፈቃደኞች አልሆኑም።+

34 ይሁንና የሚቤዣቸው ብርቱ ነው።+

ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+

ለምድሪቱ እረፍት ለመስጠትና+

የባቢሎንን ነዋሪዎች ለማሸበር+

ያላንዳች ጥርጥር ይሟገትላቸዋል።”+

35 “በከለዳውያን፣ በባቢሎን ነዋሪዎች፣ በመኳንንቷ

እንዲሁም በጥበበኞቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል” ይላል ይሖዋ።+

36 “ከንቱ ነገር በሚናገሩ ሰዎች* ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ።

በተዋጊዎቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም በሽብር ይዋጣሉ።+

37 በፈረሶቻቸው፣ በጦር ሠረገሎቻቸውና

በመካከሏ በሚኖሩ ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤

እነሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ።+

ውድ በሆኑ ሀብቶቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም ይዘረፋሉ።+

38 ውኃዎቿ ይበከላሉ፤ ይደርቃሉም።+

የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፤+

አስፈሪ በሆኑት ራእዮቻቸው የተነሳ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል።

39 ስለዚህ የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሳት ጋር ይኖራሉ፤

በእሷም ውስጥ ሰጎኖች ይኖራሉ።+

ከዚህ በኋላ የሚኖርባት አይገኝም፤

ከትውልድ እስከ ትውልድም ማንም አይቀመጥባትም።”+

40 “አምላክ ሰዶምንና ገሞራን+ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞች በደመሰሰ ጊዜ+ እንደሆነው ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+

41 እነሆ፣ አንድ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፤

አንድ ታላቅ ብሔርና ታላላቅ ነገሥታት+

ከምድር ዳርቻዎች ይነሳሉ።+

42 ቀስትና ጦር ይይዛሉ።+

ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው።+

ፈረሶቻቸውን እየጋለቡ ሲመጡ

ድምፃቸው እንደሚጮኽ ባሕር ነው።+

የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ አንቺን ለመውጋት በአንድ ልብ ሆነው ይሰለፉብሻል።+

43 የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነሱ ወሬ ሰምቷል፤+

እጆቹም ይዝለፈለፋሉ።+

ጭንቀት ይይዘዋል፤

ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ይሠቃያል።

44 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርራቸዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ።+ እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?+ 45 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በባቢሎን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና*+ በከለዳውያን ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ።

ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም።

ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+

46 ባቢሎን ስትያዝ ከሚሰማው ድምፅ የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤

ከብሔራትም መካከል ጩኸት ይሰማል።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ