የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የክርስቶስ መገኘት ምልክት (1-51)

        • ጦርነት፣ የምግብ እጥረት፣ የምድር ነውጥ (7)

        • ምሥራቹ ይሰበካል (14)

        • “ታላቅ መከራ” (21, 22)

        • የሰው ልጅ ምልክት (30)

        • የበለስ ዛፍ (32-34)

        • እንደ ኖኅ ዘመን (37-39)

        • “ነቅታችሁ ጠብቁ” (42-44)

        • ታማኙ ባሪያና ክፉው ባሪያ (45-51)

ማቴዎስ 24:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:1, 2፤ ሉቃስ 19:44፤ 21:5, 6

ማቴዎስ 24:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    ወይም “ዘመን።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 24:27, 37-39
  • +ማቴ 13:39፤ 28:20፤ ማር 13:3, 4፤ ሉቃስ 21:7

ማቴዎስ 24:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:5, 6፤ ሉቃስ 21:8

ማቴዎስ 24:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 24:24

ማቴዎስ 24:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:7፤ ሉቃስ 21:9

ማቴዎስ 24:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 6:4
  • +ሥራ 11:28፤ ራእይ 6:6
  • +ማር 13:8፤ ሉቃስ 21:10, 11

ማቴዎስ 24:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 15:20፤ ሥራ 11:19፤ ራእይ 2:10
  • +ዮሐ 16:2፤ ሥራ 7:59፤ 12:1, 2፤ ራእይ 6:11
  • +ማቴ 10:17, 22፤ ማር 13:9, 13፤ ሉቃስ 21:12, 13, 17፤ ዮሐ 15:21፤ 2ጢሞ 3:12

ማቴዎስ 24:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 7:15፤ 1ጢሞ 4:1፤ 2ጴጥ 2:1

ማቴዎስ 24:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሕገ ወጥነት።”

ማቴዎስ 24:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚጸና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:22፤ ማር 13:13፤ ሉቃስ 21:19፤ ዕብ 10:36

ማቴዎስ 24:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 9:35፤ 28:19, 20፤ ማር 13:10፤ ራእይ 14:6

ማቴዎስ 24:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 9:27፤ 11:31፤ 12:11፤ ማር 13:14-18፤ ሉቃስ 21:20

ማቴዎስ 24:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 21:21-23

ማቴዎስ 24:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በዚያ ወቅት የሚሠሩት አብዛኞቹ ቤቶች ጠፍጣፋ ጣሪያ የነበራቸው ሲሆን ሰዎች በጣሪያው ላይ የተለያዩ ሥራዎችን ያከናውኑ ነበር።

ማቴዎስ 24:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሥራ 1:12 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

ማቴዎስ 24:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 12:1፤ ማር 13:19
  • +ሉቃስ 21:23፤ ራእይ 7:14

ማቴዎስ 24:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:20

ማቴዎስ 24:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 24:5
  • +ማር 13:21-23

ማቴዎስ 24:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 7:15፤ 2ጴጥ 2:1
  • +ማቴ 7:22, 23፤ 2ተሰ 2:9

ማቴዎስ 24:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:23

ማቴዎስ 24:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:24

ማቴዎስ 24:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:37

ማቴዎስ 24:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዩ 2:31
  • +ማር 13:24, 25፤ ሉቃስ 21:25, 26

ማቴዎስ 24:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 1:7
  • +ዳን 7:13
  • +ማቴ 26:64፤ ማር 13:26፤ ሉቃስ 21:27

ማቴዎስ 24:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከሰሜን፣ ከምሥራቅ፣ ከደቡብና ከምዕራብ አቅጣጫ የሚነፍሱ ነፋሳትን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:27

ማቴዎስ 24:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በጳለስጢና ምድር ዕፀዋት የሚለመልሙት በበጋ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:28-31፤ ሉቃስ 21:29-33

ማቴዎስ 24:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ያዕ 5:8, 9

ማቴዎስ 24:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 21:33

ማቴዎስ 24:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:32፤ ሥራ 1:7
  • +1ተሰ 5:1, 2

ማቴዎስ 24:37

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 6:11-13
  • +ሉቃስ 17:26, 27

ማቴዎስ 24:38

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 7:7፤ ዕብ 11:7፤ 1ጴጥ 3:19, 20፤ 2ጴጥ 2:5

ማቴዎስ 24:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 7:23፤ 2ጴጥ 3:6

ማቴዎስ 24:41

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:35

ማቴዎስ 24:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 25:13፤ ማር 13:33፤ ሉቃስ 21:36

ማቴዎስ 24:43

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሌሊት በስንት ሰዓት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 5:2፤ 2ጴጥ 3:10
  • +ሉቃስ 12:39, 40

ማቴዎስ 24:44

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 13:35

ማቴዎስ 24:45

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጥበበኛ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 12:42-44

ማቴዎስ 24:46

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 16:15

ማቴዎስ 24:48

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 12:45, 46

ማቴዎስ 24:50

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 25:13

ማቴዎስ 24:51

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለሁለት ይቆርጠዋል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 13:42

ተዛማጅ ሐሳብ

ማቴ. 24:2ማር 13:1, 2፤ ሉቃስ 19:44፤ 21:5, 6
ማቴ. 24:3ማቴ 24:27, 37-39
ማቴ. 24:3ማቴ 13:39፤ 28:20፤ ማር 13:3, 4፤ ሉቃስ 21:7
ማቴ. 24:4ማር 13:5, 6፤ ሉቃስ 21:8
ማቴ. 24:5ማቴ 24:24
ማቴ. 24:6ማር 13:7፤ ሉቃስ 21:9
ማቴ. 24:7ራእይ 6:4
ማቴ. 24:7ሥራ 11:28፤ ራእይ 6:6
ማቴ. 24:7ማር 13:8፤ ሉቃስ 21:10, 11
ማቴ. 24:9ዮሐ 15:20፤ ሥራ 11:19፤ ራእይ 2:10
ማቴ. 24:9ዮሐ 16:2፤ ሥራ 7:59፤ 12:1, 2፤ ራእይ 6:11
ማቴ. 24:9ማቴ 10:17, 22፤ ማር 13:9, 13፤ ሉቃስ 21:12, 13, 17፤ ዮሐ 15:21፤ 2ጢሞ 3:12
ማቴ. 24:11ማቴ 7:15፤ 1ጢሞ 4:1፤ 2ጴጥ 2:1
ማቴ. 24:13ማቴ 10:22፤ ማር 13:13፤ ሉቃስ 21:19፤ ዕብ 10:36
ማቴ. 24:14ማቴ 9:35፤ 28:19, 20፤ ማር 13:10፤ ራእይ 14:6
ማቴ. 24:15ዳን 9:27፤ 11:31፤ 12:11፤ ማር 13:14-18፤ ሉቃስ 21:20
ማቴ. 24:16ሉቃስ 21:21-23
ማቴ. 24:21ዳን 12:1፤ ማር 13:19
ማቴ. 24:21ሉቃስ 21:23፤ ራእይ 7:14
ማቴ. 24:22ማር 13:20
ማቴ. 24:23ማቴ 24:5
ማቴ. 24:23ማር 13:21-23
ማቴ. 24:24ማቴ 7:15፤ 2ጴጥ 2:1
ማቴ. 24:24ማቴ 7:22, 23፤ 2ተሰ 2:9
ማቴ. 24:26ሉቃስ 17:23
ማቴ. 24:27ሉቃስ 17:24
ማቴ. 24:28ሉቃስ 17:37
ማቴ. 24:29ኢዩ 2:31
ማቴ. 24:29ማር 13:24, 25፤ ሉቃስ 21:25, 26
ማቴ. 24:30ራእይ 1:7
ማቴ. 24:30ዳን 7:13
ማቴ. 24:30ማቴ 26:64፤ ማር 13:26፤ ሉቃስ 21:27
ማቴ. 24:31ማር 13:27
ማቴ. 24:32ማር 13:28-31፤ ሉቃስ 21:29-33
ማቴ. 24:33ያዕ 5:8, 9
ማቴ. 24:35ሉቃስ 21:33
ማቴ. 24:36ማር 13:32፤ ሥራ 1:7
ማቴ. 24:361ተሰ 5:1, 2
ማቴ. 24:37ዘፍ 6:11-13
ማቴ. 24:37ሉቃስ 17:26, 27
ማቴ. 24:38ዘፍ 7:7፤ ዕብ 11:7፤ 1ጴጥ 3:19, 20፤ 2ጴጥ 2:5
ማቴ. 24:39ዘፍ 7:23፤ 2ጴጥ 3:6
ማቴ. 24:41ሉቃስ 17:35
ማቴ. 24:42ማቴ 25:13፤ ማር 13:33፤ ሉቃስ 21:36
ማቴ. 24:431ተሰ 5:2፤ 2ጴጥ 3:10
ማቴ. 24:43ሉቃስ 12:39, 40
ማቴ. 24:44ማር 13:35
ማቴ. 24:45ሉቃስ 12:42-44
ማቴ. 24:46ራእይ 16:15
ማቴ. 24:48ሉቃስ 12:45, 46
ማቴ. 24:50ማቴ 25:13
ማቴ. 24:51ማቴ 13:42
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
  • 47
  • 48
  • 49
  • 50
  • 51
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ማቴዎስ 24:1-51

የማቴዎስ ወንጌል

24 ኢየሱስ ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ እየሄደ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ወደ እሱ ቀረቡ። 2 እሱም መልሶ “ይህን ሁሉ ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ሁሉ ሳይፈርስ እንዲህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ ከቶ አይኖርም” አላቸው።+

3 በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እሱ መጥተው “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የመገኘትህና*+ የዚህ ሥርዓት* መደምደሚያ+ ምልክትስ ምንድን ነው?” አሉት።

4 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፤+ 5 ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ።+ 6 ጦርነትና የጦርነት ወሬ ትሰማላችሁ። በዚህ ጊዜ እንዳትደናገጡ ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸው የግድ ነው፤ ሆኖም ፍጻሜው ገና ነው።+

7 “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤+ በተለያየ ስፍራ የምግብ እጥረትና+ የምድር ነውጥ ይከሰታል።+ 8 እነዚህ ነገሮች ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

9 “በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፣+ ይገድሏችኋል+ እንዲሁም በስሜ ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።+ 10 በተጨማሪም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ እርስ በርሳቸውም ይጠላላሉ። 11 ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤+ 12 ክፋት* እየበዛ ስለሚሄድ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል። 13 እስከ መጨረሻው የጸና* ግን ይድናል።+ 14 ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤+ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።

15 “ስለዚህ ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’ በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ስታዩ+ አንባቢው ያስተውል፤ 16 በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።+ 17 በጣሪያ* ላይ ያለ ሰው ዕቃውን ከቤቱ ለመውሰድ አይውረድ፤ 18 በእርሻም ያለ መደረቢያውን ለመውሰድ አይመለስ። 19 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! 20 ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት* ቀን እንዳይሆን ዘወትር ጸልዩ፤ 21 ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን+ ታላቅ መከራ+ ይከሰታል። 22 እንዲያውም ቀኖቹ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ ሁሉ ባልዳነ ነበር፤ ሆኖም ለተመረጡት ሲባል ቀኖቹ ያጥራሉ።+

23 “በዚያን ጊዜ ማንም ‘እነሆ፣ ክርስቶስ ይኸውላችሁ’+ ወይም ‘ያውላችሁ’ ቢላችሁ አትመኑ።+ 24 ምክንያቱም ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤+ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያደርጋሉ።+ 25 እንግዲህ አስቀድሜ አስጠንቅቄያችኋለሁ። 26 ስለዚህ ሰዎች ‘እነሆ፣ በምድረ በዳ ነው’ ቢሏችሁ ወደዚያ አትውጡ፤ ‘እነሆ፣ ቤት ውስጥ በውስጠኛው ክፍል ይገኛል’ ቢሏችሁ አትመኑ።+ 27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚያበራ ሁሉ የሰው ልጅ መገኘትም* እንዲሁ ይሆናል።+ 28 በድን ባለበት ሁሉ ንስሮች ይሰበሰባሉ።+

29 “በእነዚያ ቀናት ከሚኖረው መከራ በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤+ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይላትም ይናወጣሉ።+ 30 ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ወገኖችም ሁሉ በሐዘን ደረታቸውን ይደቃሉ፤+ የሰው ልጅም+ በኃይልና በታላቅ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል።+ 31 እሱም መላእክቱን በታላቅ የመለከት ድምፅ ይልካል፤ እነሱም ከአራቱ ነፋሳት፣* ከአንዱ የሰማይ ዳርቻ እስከ ሌላው የሰማይ ዳርቻ ለእሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።+

32 “እንግዲያው ይህን ምሳሌ ከበለስ ዛፍ ተማሩ፦ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎቿ ሲያቆጠቁጡ በጋ* እንደቀረበ ታውቃላችሁ።+ 33 በተመሳሳይ እናንተም እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታዩ የሰው ልጅ ደጃፍ ላይ እንደደረሰ እርግጠኞች ሁኑ።+ 34 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ ፈጽሞ አያልፍም። 35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።+

36 “ስለዚያ ቀንና ሰዓት ከአብ ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ሆኑ ወልድ፣+ ማንም አያውቅም።+ 37 በኖኅ ዘመን እንደነበረው ሁሉ+ የሰው ልጅ መገኘትም* እንደዚሁ ይሆናል።+ 38 ከጥፋት ውኃ በፊት በነበረው ዘመን ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበት ቀን+ ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ወንዶች ያገቡ፣ ሴቶችም ይዳሩ ነበር፤ 39 የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም ጠራርጎ እስከወሰዳቸው ጊዜ ድረስ ምንም አላስተዋሉም፤+ የሰው ልጅ መገኘትም እንደዚሁ ይሆናል። 40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ቦታ ይሠራሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው እዚያው ይተዋል። 41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ እዚያው ትተዋለች።+ 42 ስለዚህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ ስለማታውቁ ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ።+

43 “ነገር ግን ይህን እወቁ፦ አንድ ሰው ሌባ+ በየትኛው ክፍለ ሌሊት* እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ ነቅቶ በጠበቀና ቤቱ እንዳይደፈር በተከላከለ ነበር።+ 44 ስለዚህ እናንተም የሰው ልጅ ባላሰባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ ዝግጁ ሁኑ።+

45 “በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ታማኝና ልባም* ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?+ 46 ጌታው በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው!+ 47 እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል።

48 “ነገር ግን ያ ክፉ ባሪያ በልቡ ‘ጌታዬ ይዘገያል’ ብሎ ቢያስብ+ 49 ደግሞም ባልንጀሮቹ የሆኑትን ባሪያዎች መደብደብ ቢጀምር እንዲሁም ከሰካራሞች ጋር ቢበላና ቢጠጣ፣ 50 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ይመጣል፤+ 51 ከባድ ቅጣት ይቀጣዋል፤* ዕጣውንም ከግብዞች ጋር ያደርገዋል። በዚያም ያለቅሳል፤ ጥርሱንም ያፋጫል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ