የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • የሞሎክ አምልኮ፤ መናፍስታዊ ድርጊት (1-6)

      • ቅዱሳን ሁኑ፤ ወላጆቻችሁን አክብሩ (7-9)

      • ተገቢ ያልሆነ የፆታ ግንኙነት የፈጸሙ በሞት ይቀጣሉ (10-21)

      • በምድሪቱ ለመኖር ቅዱሳን ሁኑ (22-26)

      • መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ በሞት ይቀጣሉ (27)

ዘሌዋውያን 20:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:21፤ ዘዳ 18:10

ዘሌዋውያን 20:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 5:11

ዘሌዋውያን 20:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 13:6-9

ዘሌዋውያን 20:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:5

ዘሌዋውያን 20:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:31፤ ዘዳ 18:10-12፤ ገላ 5:19, 20፤ ራእይ 21:8
  • +ዘሌ 20:27፤ ሥራ 16:16
  • +1ዜና 10:13

ዘሌዋውያን 20:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:44፤ 1ጴጥ 1:15, 16

ዘሌዋውያን 20:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:4፤ መክ 12:13
  • +ዘፀ 31:13፤ ዘሌ 21:8፤ 1ተሰ 5:23፤ 2ተሰ 2:13

ዘሌዋውያን 20:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:17፤ ዘዳ 27:16፤ ምሳሌ 20:20፤ ማቴ 15:4

ዘሌዋውያን 20:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:18፤ 22:22፤ ሮም 7:3፤ 1ቆሮ 6:9, 10

ዘሌዋውያን 20:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የአባቱን እርቃን ገልጧል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:8፤ ዘዳ 27:20

ዘሌዋውያን 20:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:15, 29

ዘሌዋውያን 20:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 19:5፤ ዘሌ 18:22፤ መሳ 19:22፤ ሮም 1:26, 27፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ ይሁዳ 7

ዘሌዋውያን 20:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሳፋሪ ምግባር፤ ሴሰኝነት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:17፤ ዘዳ 27:23
  • +ዘሌ 21:9

ዘሌዋውያን 20:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:19፤ ዘዳ 27:21

ዘሌዋውያን 20:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:23

ዘሌዋውያን 20:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የእህቱን እርቃን ገልጧል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:9፤ ዘዳ 27:22

ዘሌዋውያን 20:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:19

ዘሌዋውያን 20:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:12, 13

ዘሌዋውያን 20:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የአጎቱን እርቃን ገልጧል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:14

ዘሌዋውያን 20:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የወንድሙን እርቃን ገልጧል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:16፤ ዘዳ 25:5

ዘሌዋውያን 20:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:26, 28
  • +ዘፀ 21:1፤ ዘዳ 5:1
  • +መክ 12:13

ዘሌዋውያን 20:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:3, 24፤ ዘዳ 12:30
  • +ዘሌ 18:27፤ ዘዳ 9:5

ዘሌዋውያን 20:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:17፤ 6:8፤ ዘዳ 8:7-9፤ ሕዝ 20:6
  • +ዘፀ 19:5፤ 33:16፤ 1ነገ 8:53፤ 1ጴጥ 2:9

ዘሌዋውያን 20:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችሁን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 11:46, 47፤ ዘዳ 14:4-20
  • +ዘሌ 11:43

ዘሌዋውያን 20:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:2፤ መዝ 99:5፤ 1ጴጥ 1:15, 16፤ ራእይ 4:8
  • +ዘዳ 7:6

ዘሌዋውያን 20:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:18፤ ዘሌ 19:31፤ 20:6፤ ዘዳ 18:10-12፤ ራእይ 21:8

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 20:2ዘሌ 18:21፤ ዘዳ 18:10
ዘሌ. 20:3ሕዝ 5:11
ዘሌ. 20:4ዘዳ 13:6-9
ዘሌ. 20:5ዘፀ 20:5
ዘሌ. 20:6ዘሌ 19:31፤ ዘዳ 18:10-12፤ ገላ 5:19, 20፤ ራእይ 21:8
ዘሌ. 20:6ዘሌ 20:27፤ ሥራ 16:16
ዘሌ. 20:61ዜና 10:13
ዘሌ. 20:7ዘሌ 11:44፤ 1ጴጥ 1:15, 16
ዘሌ. 20:8ዘሌ 18:4፤ መክ 12:13
ዘሌ. 20:8ዘፀ 31:13፤ ዘሌ 21:8፤ 1ተሰ 5:23፤ 2ተሰ 2:13
ዘሌ. 20:9ዘፀ 21:17፤ ዘዳ 27:16፤ ምሳሌ 20:20፤ ማቴ 15:4
ዘሌ. 20:10ዘዳ 5:18፤ 22:22፤ ሮም 7:3፤ 1ቆሮ 6:9, 10
ዘሌ. 20:11ዘሌ 18:8፤ ዘዳ 27:20
ዘሌ. 20:12ዘሌ 18:15, 29
ዘሌ. 20:13ዘፍ 19:5፤ ዘሌ 18:22፤ መሳ 19:22፤ ሮም 1:26, 27፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ ይሁዳ 7
ዘሌ. 20:14ዘሌ 18:17፤ ዘዳ 27:23
ዘሌ. 20:14ዘሌ 21:9
ዘሌ. 20:15ዘፀ 22:19፤ ዘዳ 27:21
ዘሌ. 20:16ዘሌ 18:23
ዘሌ. 20:17ዘሌ 18:9፤ ዘዳ 27:22
ዘሌ. 20:18ዘሌ 18:19
ዘሌ. 20:19ዘሌ 18:12, 13
ዘሌ. 20:20ዘሌ 18:14
ዘሌ. 20:21ዘሌ 18:16፤ ዘዳ 25:5
ዘሌ. 20:22ዘሌ 18:26, 28
ዘሌ. 20:22ዘፀ 21:1፤ ዘዳ 5:1
ዘሌ. 20:22መክ 12:13
ዘሌ. 20:23ዘሌ 18:3, 24፤ ዘዳ 12:30
ዘሌ. 20:23ዘሌ 18:27፤ ዘዳ 9:5
ዘሌ. 20:24ዘፀ 3:17፤ 6:8፤ ዘዳ 8:7-9፤ ሕዝ 20:6
ዘሌ. 20:24ዘፀ 19:5፤ 33:16፤ 1ነገ 8:53፤ 1ጴጥ 2:9
ዘሌ. 20:25ዘሌ 11:46, 47፤ ዘዳ 14:4-20
ዘሌ. 20:25ዘሌ 11:43
ዘሌ. 20:26ዘሌ 19:2፤ መዝ 99:5፤ 1ጴጥ 1:15, 16፤ ራእይ 4:8
ዘሌ. 20:26ዘዳ 7:6
ዘሌ. 20:27ዘፀ 22:18፤ ዘሌ 19:31፤ 20:6፤ ዘዳ 18:10-12፤ ራእይ 21:8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 20:1-27

ዘሌዋውያን

20 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ልጁን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም እስራኤል ውስጥ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ይገደል።+ የአገሩ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉት። 3 ልጆቹን ለሞሎክ ስለሰጠ እንዲሁም ቅዱሱን ስፍራዬን ስላረከሰና+ ቅዱሱን ስሜን ስላቃለለ እኔ ራሴ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 4 የአገሩ ሰዎች ሰውየው ልጁን ለሞሎክ በመስጠት የፈጸመውን ድርጊት አይተው እንዳላዩ ቢሆኑና ሳይገድሉት ቢቀሩ+ 5 እኔ ራሴ በዚህ ሰውና በቤተሰቡ ላይ እነሳባቸዋለሁ።+ ያንን ሰውም ሆነ ከሞሎክ ጋር ምንዝር በመፈጸም የእሱን ፈለግ የተከተሉትን ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋቸዋለሁ።

6 “‘አንድ ሰው* ከመናፍስት ጠሪዎችና+ ከጠንቋዮች+ ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ወደ እነሱ ቢሄድ እኔ በዚያ ሰው* ላይ በእርግጥ እነሳበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።+

7 “‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆንኩ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ።+ 8 ደንቦቼን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ።+

9 “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል።+ አባቱን ወይም እናቱን ስለረገመ ደሙ በራሱ ላይ ነው።

10 “‘ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽምን ሰው በተመለከተ እንዲህ ይደረግ፦ ከባልንጀራው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሰው ይገደል፤ አመንዝራውም ሆነ አመንዝራይቱ ይገደሉ።+ 11 ከአባቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አባቱን ለኀፍረት ዳርጎታል።*+ ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። 12 አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ ሁለቱም ይገደሉ። ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ድርጊት ፈጽመዋል። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።+

13 “‘አንድ ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱም አስጸያፊ ድርጊት ፈጽመዋል።+ ስለዚህ ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

14 “‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ ይህ ጸያፍ ድርጊት* ነው።+ ይህ ጸያፍ ምግባር በመካከላችሁ እንዳይቀጥል እሱንም ሆነ እነሱን በእሳት ያቃጥሏቸው።+

15 “‘አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም ይገደል፤ እንስሳውንም ግደሉት።+ 16 አንዲት ሴት የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም እንስሳ ብትቀርብ+ ሴትየዋንም ሆነ እንስሳውን ግደል፤ ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

17 “‘አንድ ሰው ከእህቱ ማለትም ከአባቱ ሴት ልጅ ወይም ከእናቱ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽምና እርቃኗን ቢያይ፣ እሷም የእሱን እርቃን ብታይ ይህ አሳፋሪ ድርጊት ነው።+ በሕዝቦቻቸው ልጆች ፊት እንዲጠፉ ይደረጉ። እህቱን ለኀፍረት ዳርጓል።* ለፈጸመው ጥፋት ይጠየቅበታል።

18 “‘አንድ ሰው በወር አበባዋ ወቅት ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም እሱም ሆነ እሷ የሚፈሰውን ደሟን ገልጠዋል።+ ስለሆነም ሁለቱም ከሕዝቦቻቸው መካከል ተለይተው እንዲጠፉ ይደረጉ።

19 “‘ከእናትህ እህት ወይም ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም ይህ የሥጋ ዘመድን ለኀፍረት መዳረግ ነው።+ ለፈጸሙት ጥፋት ይጠየቁበታል። 20 ከአጎቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አጎቱን ለኀፍረት ዳርጓል።*+ ለፈጸሙት ኃጢአት ይጠየቁበታል። ልጅ ሳይኖራቸው ይሙቱ። 21 አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢወስድ ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው።+ ወንድሙን ለኀፍረት ዳርጓል።* ያለልጅም ይቅሩ።

22 “‘ትኖሩባት ዘንድ እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ+ ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ሁሉ ጠብቁ፤+ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ 23 ከፊታችሁ አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት በሚመሩባቸው ደንቦች አትሂዱ፤+ ምክንያቱም እነሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፤ እኔም እጸየፋቸዋለሁ።+ 24 በመሆኑም እንዲህ አልኳችሁ፦ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እኔ ደግሞ ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር+ እንድትወርሷት እሰጣችኋለሁ። ከሕዝቦች የለየኋችሁ አምላካችሁ ይሖዋ እኔ ነኝ።”+ 25 ንጹሕ በሆነውና ርኩስ በሆነው እንስሳ እንዲሁም ርኩስ በሆነውና ንጹሕ በሆነው ወፍ መካከል ልዩነት አድርጉ፤+ እኔ ርኩስ ነው ብዬ በለየሁላችሁ እንስሳ ወይም ወፍ አሊያም መሬት ለመሬት በሚሄድ ማንኛውም ነገር ራሳችሁን* አታርክሱ።+ 26 እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ለእኔ ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል፤+ የእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ሕዝቦች ለየኋችሁ።+

27 “‘መናፍስት ጠሪ ወይም ጠንቋይ የሆነ ወንድ ወይም የሆነች ሴት ካሉ ይገደሉ።+ ሕዝቡ በድንጋይ ወግሮ ይግደላቸው። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ