የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘኁልቁ የመጽሐፉ ይዘት

      • አሥራ ሁለቱ ሰላዮች ወደ ከነአን ተላኩ (1-24)

      • አሥሩ ሰላዮች ያመጡት መጥፎ ወሬ (25-33)

ዘኁልቁ 13:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:25፤ ዘዳ 1:15
  • +ዘዳ 1:22, 23

ዘኁልቁ 13:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 12:16፤ ዘዳ 1:19

ዘኁልቁ 13:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:30፤ 14:30, 38፤ 34:18, 19፤ 1ዜና 4:15

ዘኁልቁ 13:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 11:28፤ 13:16፤ 14:30፤ 34:17

ዘኁልቁ 13:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 48:5
  • +ዘፍ 48:17, 19

ዘኁልቁ 13:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሆሹአ።” “ይሖዋ አዳኝ ነው” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 17:9

ዘኁልቁ 13:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 1:7

ዘኁልቁ 13:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7

ዘኁልቁ 13:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሰባች።”

  • *

    ቃል በቃል “ያልሰባች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:25፤ ሕዝ 20:6
  • +ዘዳ 31:6፤ ኢያሱ 1:6, 9
  • +ዘኁ 13:23

ዘኁልቁ 13:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሃማት መግቢያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 34:2, 3፤ ኢያሱ 15:1
  • +ዘኁ 34:8
  • +2ሳሙ 10:6, 8

ዘኁልቁ 13:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 9:1, 2፤ ኢያሱ 11:21
  • +መሳ 1:10
  • +ዘፍ 13:18፤ ኢያሱ 15:13፤ 21:11, 12

ዘኁልቁ 13:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 32:9
  • +ዘዳ 1:25፤ 8:7-9

ዘኁልቁ 13:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የወይን ዘለላ” የሚል ትርጉም አለው።

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 1:24

ዘኁልቁ 13:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:33, 34

ዘኁልቁ 13:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 1:19

ዘኁልቁ 13:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:8፤ ዘሌ 20:24
  • +ዘዳ 1:25

ዘኁልቁ 13:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:22, 33፤ ዘዳ 1:27, 28

ዘኁልቁ 13:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 36:12፤ ዘፀ 17:8፤ 1ሳሙ 15:3
  • +ዘኁ 13:17
  • +መሳ 1:21፤ 2ሳሙ 5:6, 7
  • +ዘፍ 10:15, 16
  • +ዘፍ 10:19
  • +ዘፀ 23:23፤ ዘዳ 7:1፤ 20:17

ዘኁልቁ 13:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 14:7, 8

ዘኁልቁ 13:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 32:9

ዘኁልቁ 13:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:36
  • +አሞጽ 2:9

ዘኁልቁ 13:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 1:28፤ 9:1, 2

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘኁ. 13:2ዘፀ 18:25፤ ዘዳ 1:15
ዘኁ. 13:2ዘዳ 1:22, 23
ዘኁ. 13:3ዘኁ 12:16፤ ዘዳ 1:19
ዘኁ. 13:6ዘኁ 13:30፤ 14:30, 38፤ 34:18, 19፤ 1ዜና 4:15
ዘኁ. 13:8ዘኁ 11:28፤ 13:16፤ 14:30፤ 34:17
ዘኁ. 13:11ዘፍ 48:5
ዘኁ. 13:11ዘፍ 48:17, 19
ዘኁ. 13:16ዘፀ 17:9
ዘኁ. 13:17ዘዳ 1:7
ዘኁ. 13:18ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7
ዘኁ. 13:20ነህ 9:25፤ ሕዝ 20:6
ዘኁ. 13:20ዘዳ 31:6፤ ኢያሱ 1:6, 9
ዘኁ. 13:20ዘኁ 13:23
ዘኁ. 13:21ዘኁ 34:2, 3፤ ኢያሱ 15:1
ዘኁ. 13:21ዘኁ 34:8
ዘኁ. 13:212ሳሙ 10:6, 8
ዘኁ. 13:22ዘዳ 9:1, 2፤ ኢያሱ 11:21
ዘኁ. 13:22መሳ 1:10
ዘኁ. 13:22ዘፍ 13:18፤ ኢያሱ 15:13፤ 21:11, 12
ዘኁ. 13:23ዘኁ 32:9
ዘኁ. 13:23ዘዳ 1:25፤ 8:7-9
ዘኁ. 13:24ዘዳ 1:24
ዘኁ. 13:25ዘኁ 14:33, 34
ዘኁ. 13:26ዘዳ 1:19
ዘኁ. 13:27ዘፀ 3:8፤ ዘሌ 20:24
ዘኁ. 13:27ዘዳ 1:25
ዘኁ. 13:28ዘኁ 13:22, 33፤ ዘዳ 1:27, 28
ዘኁ. 13:29ዘፍ 36:12፤ ዘፀ 17:8፤ 1ሳሙ 15:3
ዘኁ. 13:29ዘኁ 13:17
ዘኁ. 13:29መሳ 1:21፤ 2ሳሙ 5:6, 7
ዘኁ. 13:29ዘፍ 10:15, 16
ዘኁ. 13:29ዘፍ 10:19
ዘኁ. 13:29ዘፀ 23:23፤ ዘዳ 7:1፤ 20:17
ዘኁ. 13:30ኢያሱ 14:7, 8
ዘኁ. 13:31ዘኁ 32:9
ዘኁ. 13:32ዘኁ 14:36
ዘኁ. 13:32አሞጽ 2:9
ዘኁ. 13:33ዘዳ 1:28፤ 9:1, 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘኁልቁ 13:1-33

ዘኁልቁ

13 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ። ከእያንዳንዱ የአባቶች ነገድ አንድ አንድ ሰው ይኸውም ከመካከላቸው አለቃ+ የሆነውን ሰው ትልካለህ።”+

3 በመሆኑም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ከፋራን ምድረ በዳ+ ላካቸው። ሰዎቹ በሙሉ የእስራኤላውያን መሪዎች ነበሩ። 4 ስማቸውም የሚከተለው ነው፦ ከሮቤል ነገድ የዛኩር ልጅ ሻሙአ፣ 5 ከስምዖን ነገድ የሆሪ ልጅ ሻፋጥ፣ 6 ከይሁዳ ነገድ የየፎኒ ልጅ ካሌብ፣+ 7 ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግዓል፣ 8 ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሺአ፣+ 9 ከቢንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፓልጢ፣ 10 ከዛብሎን ነገድ የሶዲ ልጅ ጋዲኤል፣ 11 ከዮሴፍ+ ነገድ መካከል ለምናሴ+ ነገድ የሱሲ ልጅ ጋዲ፣ 12 ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ አሚዔል፣ 13 ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፣ 14 ከንፍታሌም ነገድ የዎፍሲ ልጅ ናህቢ 15 እንዲሁም ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጌኡዔል። 16 ሙሴ ምድሪቱን እንዲሰልሉ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም ለነዌ ልጅ ለሆሺአ፣ ኢያሱ*+ የሚል ስም አወጣለት።

17 ሙሴ የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎቹን ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በዚህ አድርጋችሁ ወደ ኔጌብ አቅኑ፤ ከዚያም ወደ ተራራማው አካባቢ ሂዱ።+ 18 ምድሪቱ ምን እንደምትመስል፣+ ነዋሪዎቿም ብርቱ ወይም ደካማ፣ ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን እዩ፤ 19 እንዲሁም ምድሪቱ መልካም ወይም መጥፎ መሆኗን ከተሞቹም በግንብ የታጠሩ ወይም ያልታጠሩ መሆናቸውን ተመልከቱ። 20 ምድሪቱም ለም* ወይም ደረቅ* መሆኗን፣+ በዚያም ዛፎች መኖር አለመኖራቸውን አጣሩ። እንዲሁም በድፍረት+ ከምድሪቱ ፍሬ ጥቂት ይዛችሁ ኑ።” ደግሞም ጊዜው የመጀመሪያው የወይን ፍሬ የሚደርስበት ወቅት ነበር።+

21 ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ምድሪቱን ከጺን ምድረ በዳ+ አንስተው በሌቦሃማት*+ አቅራቢያ እስከምትገኘው እስከ ሬሆብ+ ድረስ ሰለሉ። 22 በኔጌብ በኩል ሽቅብ ሲወጡም ኤናቃውያኑ+ አሂማን፣ ሸሻይ እና ታልማይ+ ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን+ ደረሱ። ኬብሮን የተቆረቆረችው በግብፅ ያለችው ጾዓን ከመቆርቆሯ ከሰባት ዓመት በፊት ነበር። 23 ወደ ኤሽኮል ሸለቆ*+ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላዎችን ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ከዚያ ቆረጡ፤ ከሰዎቹም መካከል ሁለቱ በዱላ ተሸከሙት፤ በተጨማሪም ጥቂት የሮማን ፍሬዎችንና የበለስ ፍሬዎችን ያዙ።+ 24 እስራኤላውያን ከዚያ በቆረጡት ዘለላ የተነሳ ያን ቦታ የኤሽኮል* ሸለቆ*+ ብለው ጠሩት።

25 ምድሪቱንም ሰልለው ከ40 ቀን+ በኋላ ተመለሱ። 26 በቃዴስ+ ባለው በፋራን ምድረ በዳ ወደሚገኙት ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ተመልሰው መጡ። ያዩትንም ሁሉ ለመላው ማኅበረሰብ ተናገሩ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው። 27 ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “ወደላክኸን ምድር ገብተን ነበር፤ በእርግጥም ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፤+ የምድሪቱም ፍሬ+ ይህን ይመስላል። 28 ይሁንና በምድሪቱ የሚኖሩት ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤ በግንብ የታጠሩት ከተሞችም ቢሆኑ በጣም ታላላቅ ናቸው። ደግሞም ኤናቃውያንን በዚያ አይተናል።+ 29 አማሌቃውያን+ በኔጌብ+ ምድር ይኖራሉ፤ ሂታውያን፣ ኢያቡሳውያንና+ አሞራውያን+ ደግሞ በተራራማው አካባቢ ይኖራሉ፤ በባሕሩ አካባቢና+ በዮርዳኖስ ዳርቻ ደግሞ ከነአናውያን+ ይኖራሉ።”

30 ከዚያም ካሌብ “በድፍረት እንውጣ፤ ድል እንደምናደርግ ምንም ጥርጥር ስለሌለው ምድሪቱን እንወርሳለን” በማለት በሙሴ ፊት የቆመውን ሕዝብ ሊያረጋጋ ሞከረ።+ 31 ከእሱ ጋር የወጡት ሰዎች ግን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለሆኑ ወጥተን ልንዋጋቸው አንችልም” አሉ።+ 32 እንዲሁም የሰለሏትን ምድር በተመለከተ ለእስራኤላውያን እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ+ አወሩ፦ “በውስጧ ተዘዋውረን የሰለልናት ምድር ነዋሪዎቿን የምትበላ ምድር ናት፤ እዚያ ያየናቸውም ሰዎች በሙሉ እጅግ ግዙፎች ናቸው።+ 33 በዚያም ኔፍሊምን ይኸውም የኔፍሊም ዝርያ የሆኑትን የኤናቅን ልጆች+ አይተናል፤ እኛ ከእነሱ ጋር ስንነጻጸር በእኛም ሆነ በእነሱ ዓይን ልክ እንደ ፌንጣ ነበርን።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ