የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 27
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • በስእለት የተሰጡ ነገሮችን መዋጀት (1-27)

        • ሰዎችን (1-8)

        • እንስሳትን (9-13)

        • ቤትን (14, 15)

        • እርሻን (16-25)

        • በኩርን (26, 27)

      • ሊዋጁ የማይችሉ ለይሖዋ የተሰጡ ነገሮች (28, 29)

      • አንድ አሥረኛ ተደርገው የተሰጡ ነገሮችን መዋጀት (30-34)

ዘሌዋውያን 27:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 23:21፤ መሳ 11:30, 31፤ 1ሳሙ 1:11

ዘሌዋውያን 27:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቅዱሱ ሰቅል።”

  • *

    አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘሌዋውያን 27:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 5:7, 11፤ 12:8፤ 14:21
  • +ሉቃስ 21:2-4፤ 2ቆሮ 8:12

ዘሌዋውያን 27:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:25፤ ዘዳ 14:7, 8

ዘሌዋውያን 27:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:19

ዘሌዋውያን 27:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:11, 12

ዘሌዋውያን 27:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ሆሜር 220 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘሌዋውያን 27:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:10

ዘሌዋውያን 27:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:15, 16

ዘሌዋውያን 27:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:8, 14

ዘሌዋውያን 27:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:25

ዘሌዋውያን 27:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:11, 12, 18

ዘሌዋውያን 27:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:10, 28

ዘሌዋውያን 27:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ጌራ 0.57 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘሌዋውያን 27:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:2፤ ዘኁ 18:17
  • +ዘፀ 22:30፤ ዘዳ 15:19

ዘሌዋውያን 27:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:11-13

ዘሌዋውያን 27:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:8, 14

ዘሌዋውያን 27:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 21:2
  • +ኢያሱ 6:17፤ 1ሳሙ 15:3, 18

ዘሌዋውያን 27:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሥራት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 14:20፤ 28:22፤ ዘኁ 18:21, 26፤ ዘዳ 14:22፤ 2ዜና 31:5፤ ነህ 13:12፤ ሚል 3:10፤ ሉቃስ 11:42፤ ዕብ 7:5

ዘሌዋውያን 27:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ራስ።”

ዘሌዋውያን 27:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:9, 10

ዘሌዋውያን 27:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:1፤ ዘኁ 1:1

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 27:2ዘዳ 23:21፤ መሳ 11:30, 31፤ 1ሳሙ 1:11
ዘሌ. 27:8ዘሌ 5:7, 11፤ 12:8፤ 14:21
ዘሌ. 27:8ሉቃስ 21:2-4፤ 2ቆሮ 8:12
ዘሌ. 27:11ዘሌ 20:25፤ ዘዳ 14:7, 8
ዘሌ. 27:13ዘሌ 27:19
ዘሌ. 27:14ዘሌ 27:11, 12
ዘሌ. 27:17ዘሌ 25:10
ዘሌ. 27:18ዘሌ 25:15, 16
ዘሌ. 27:21ዘኁ 18:8, 14
ዘሌ. 27:22ዘሌ 25:25
ዘሌ. 27:23ዘሌ 27:11, 12, 18
ዘሌ. 27:24ዘሌ 25:10, 28
ዘሌ. 27:26ዘፀ 13:2፤ ዘኁ 18:17
ዘሌ. 27:26ዘፀ 22:30፤ ዘዳ 15:19
ዘሌ. 27:27ዘሌ 27:11-13
ዘሌ. 27:28ዘኁ 18:8, 14
ዘሌ. 27:29ዘኁ 21:2
ዘሌ. 27:29ኢያሱ 6:17፤ 1ሳሙ 15:3, 18
ዘሌ. 27:30ዘፍ 14:20፤ 28:22፤ ዘኁ 18:21, 26፤ ዘዳ 14:22፤ 2ዜና 31:5፤ ነህ 13:12፤ ሚል 3:10፤ ሉቃስ 11:42፤ ዕብ 7:5
ዘሌ. 27:33ዘሌ 27:9, 10
ዘሌ. 27:34ዘፀ 3:1፤ ዘኁ 1:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 27:1-34

ዘሌዋውያን

27 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አንድ ሰው የአንድን ግለሰብ* የተተመነ ዋጋ ለይሖዋ ለማቅረብ ልዩ ስእለት ቢሳል+ 3 ከ20 ዓመት እስከ 60 ዓመት ድረስ ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኝ ወንድ የሚተመነው ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* 50 የብር ሰቅል* ይሆናል። 4 ሴት ከሆነች ግን የሚተመንላት ዋጋ 30 ሰቅል ይሆናል። 5 ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ 20 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ 10 ሰቅል ይሆናል። 6 ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ አምስት የብር ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ ሦስት የብር ሰቅል ይሆናል።

7 “‘ዕድሜው ከ60 ዓመት በላይ ለሆነ ወንድ ደግሞ የሚተመንለት ዋጋ 15 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች 10 ሰቅል ይሆናል። 8 ሆኖም ሰውየው በጣም ድሃ ቢሆንና የተተመነውን ዋጋ መስጠት ባይችል+ ግለሰቡ ካህኑ ፊት ይቆማል፤ ካህኑም ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል። ካህኑ ስእለት የተሳለውን ሰው አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል።+

9 “‘ስእለቱ ለይሖዋ መባ ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ ለይሖዋ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር የተቀደሰ ይሆናል። 10 እንስሳውን በሌላ መተካትም ሆነ መጥፎውን በጥሩ፣ ጥሩውን በመጥፎ መለወጥ አይችልም። እንስሳውን በሌላ እንስሳ መለወጥ ካለበት ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ። 11 ሰውየው ያቀረበው እንስሳ ለይሖዋ መባ ሆኖ ሊቀርብ የማይችል ርኩስ እንስሳ+ ከሆነ እንስሳውን ካህኑ ፊት ያቁመው። 12 ካህኑ እንስሳው ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። ካህኑ የተመነውም ዋጋ ይጸናል። 13 ሆኖም ሰውየው እንስሳውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት።+

14 “‘አንድ ሰው ቤቱን ቅዱስ አድርጎ ለይሖዋ ቢሰጥ ካህኑ ቤቱ ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። የቤቱ ዋጋ ካህኑ የተመነው ዋጋ ይሆናል።+ 15 ሆኖም ቤቱን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው ቤቱን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ቤቱም የእሱ ይሆናል።

16 “‘አንድ ሰው ርስት አድርጎ ከያዘው እርሻ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ ዋጋው መተመን ያለበት የሚዘራበትን ዘር መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል፤ ለአንድ ሆሜር* የገብስ ዘር 50 የብር ሰቅል ይሆናል። 17 ሰውየው እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት+ አንስቶ ቅዱስ አድርጎ ከሰጠ የተተመነለት ዋጋ ይጸናል። 18 ሰውየው እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ኢዮቤልዩ ካለፈ በኋላ ከሆነ ካህኑ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የቀሩትን ዓመታት ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋውን ያስላለት፤ ከተተመነውም ዋጋ ላይ መቀነስ አለበት።+ 19 ሆኖም እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው እርሻውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ከዚያም እርሻው የእሱ ንብረት እንደሆነ ይጸናል። 20 ሰውየው እርሻውን መልሶ ባይገዛውና እርሻው ለሌላ ሰው ቢሸጥ ሰውየው መልሶ ሊገዛው አይችልም። 21 እርሻው በኢዮቤልዩ ነፃ በሚለቀቅበት ጊዜ ለይሖዋ እንደተሰጠ እርሻ ተቆጥሮ ለእሱ የተቀደሰ ይሆናል። የካህናቱም ንብረት ይሆናል።+

22 “‘አንድ ሰው በውርስ ያገኘው ንብረት ክፍል ያልሆነውን በገንዘቡ የገዛውን እርሻ+ ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ 23 ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የሚያወጣውን ዋጋ ይተምንለት፤ እሱም የተተመነውን ዋጋ በዚያው ቀን ይስጥ።+ ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። 24 በኢዮቤልዩ ዓመት እርሻው ለሻጩ ይኸውም ለመሬቱ ባለቤት ይመለሳል።+

25 “‘እያንዳንዱ ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት መተመን አለበት። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ* መሆን ይኖርበታል።

26 “‘ይሁንና ማንም ሰው ከእንስሳት መካከል በኩር የሆነውን ቅዱስ አድርጎ መስጠት የለበትም፤ ምክንያቱም በኩሩ የይሖዋ ነው።+ በሬም ሆነ በግ ቀድሞውንም የይሖዋ ነው።+ 27 በኩሩ ርኩስ ከሆኑት እንስሳት መካከል ከሆነና በተተመነለት ዋጋ መሠረት ከዋጀው በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት።+ ሰውየው መልሶ የማይገዛው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ መሠረት ይሸጥ።

28 “‘አንድ ሰው የራሱ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ ያለምንም ገደብ ለይሖዋ የሰጠው ማንኛውም ተለይቶ የተሰጠ ነገር ይኸውም የእሱ ንብረት የሆነ ሰውም ሆነ እንስሳ አሊያም እርሻ ሊሸጥም ሆነ ተመልሶ ሊገዛ አይችልም። ተለይቶ የተሰጠ ማንኛውም ነገር ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው።+ 29 በተጨማሪም እንዲጠፋ የተበየነበት ማንኛውም ለጥፋት የተለየ ሰው አይዋጅም፤+ ከዚህ ይልቅ መገደል አለበት።+

30 “‘እርሻው ከሚሰጠው ምርትም ሆነ ዛፉ ከሚያፈራው ፍሬ ውስጥ የምድሩ አንድ አሥረኛ*+ ሁሉ የይሖዋ ነው። ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። 31 አንድ ሰው አንድ አሥረኛ አድርጎ የሰጠውን ማንኛውንም ነገር መልሶ መግዛት ቢፈልግ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። 32 ከከብቶቹና ከመንጋው መካከል አንድ አሥረኛው ማለትም በበትሩ ሥር ከሚያልፉት መካከል አሥረኛው እንስሳ* ለይሖዋ የተቀደሰ መሆን አለበት። 33 ከዚህ በኋላ እንስሳው ጥሩ ይሁን መጥፎ መመርመር የለበትም፤ በሌላ ሊለውጠውም አይገባም። እንስሳውን በሌላ መለወጥ ካሰበ ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ።+ ተመልሶ ሊገዛ አይችልም።’”

34 ይሖዋ በሲና ተራራ+ ላይ በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ