ምሳሌ
31 የንጉሥ ልሙኤል ቃል፤ እናቱ እሱን ለማስተማር የተናገረችው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት፦+
5 አለዚያ ጠጥተው የተደነገገውን ሕግ ይረሳሉ፤
የችግረኞችንም መብት ይጥሳሉ።
7 ጠጥተው ድህነታቸውን ይርሱ፤
ችግራቸውንም ዳግመኛ አያስታውሱ።
8 ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት አንተ ተናገርላቸው፤
ሊጠፉ ለተቃረቡት ሰዎች ሁሉ መብት ተሟገት።+
א [አሌፍ]
ዋጋዋ ከዛጎል* እጅግ ይበልጣል።
ב [ቤት]
11 ባሏ ከልቡ ይታመንባታል፤
አንዳችም ጠቃሚ ነገር አይጎድልበትም።
ג [ጊሜል]
12 በሕይወቷ ዘመን ሁሉ
መልካም ነገር ታደርግለታለች እንጂ ክፉ ነገር አታደርግበትም።
ד [ዳሌት]
13 ሱፍና በፍታ ታመጣለች፤
በእጆቿ መሥራት ያስደስታታል።+
ה [ሄ]
14 እሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤+
ምግቧን ከሩቅ ቦታ ታመጣለች።
ו [ዋው]
ז [ዛየን]
16 በጥሞና ካሰበችበት በኋላ መሬት ትገዛለች፤
በራሷ ጥረት* ወይን ትተክላለች።
ח [ኼት]
ט [ቴት]
18 ንግዷ ትርፋማ እንደሆነ ታስተውላለች፤
መብራቷ በሌሊት አይጠፋም።
י [ዮድ]
כ [ካፍ]
20 እጆቿን ለተቸገረ ሰው ትዘረጋለች፤
ለድሃውም እጇን ትከፍታለች።+
ל [ላሜድ]
21 ቤተሰቦቿ ሁሉ የሚያሞቅ* ልብስ ስለሚለብሱ
በበረዶ ወቅት እንኳ አትሰጋም።
מ [ሜም]
22 ለራሷ የአልጋ ልብስ ትሠራለች።
ልብሷ ከበፍታና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው።
נ [ኑን]
23 ባሏ ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር በሚቀመጥበት በከተማዋ በሮች+
በሰዎች ዘንድ በሰፊው የታወቀ ነው።
ס [ሳሜኽ]
24 የበፍታ ልብሶች እየሠራች* ትሸጣለች፤
ለነጋዴዎችም ቀበቶ ታስረክባለች።
ע [አይን]
25 ብርታትንና ግርማን ትጎናጸፋለች፤
የወደፊቱንም ጊዜ በልበ ሙሉነት ትጠባበቃለች።*
פ [ፔ]
צ [ጻዴ]
27 የቤተሰቧን እንቅስቃሴ በደንብ ትከታተላለች፤
የስንፍናንም ምግብ አትበላም።+
ק [ኮፍ]
28 ልጆቿ ተነስተው ደስተኛ ይሏታል፤
ባሏ ተነስቶ ያወድሳታል።
ר [ረሽ]
29 ባለሙያ* የሆኑ ብዙ ሴቶች አሉ፤
አንቺ ግን፣ አዎ አንቺ ከሁሉም ትበልጫለሽ።
ש [ሺን]
ת [ታው]