የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መሳፍንት 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መሳፍንት የመጽሐፉ ይዘት

      • የሚክያስ ጣዖታትና ካህኑ (1-13)

መሳፍንት 17:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 17:14, 15

መሳፍንት 17:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:4፤ ዘሌ 26:1፤ ዘዳ 27:15

መሳፍንት 17:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልት።”

መሳፍንት 17:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤት ውስጥ አማልክት፤ ጣዖታት።”

  • *

    ቃል በቃል “እጁን ሞላው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 28:6፤ መሳ 8:27
  • +ዘፍ 31:19
  • +ዘኁ 3:10፤ ዘዳ 12:11, 13፤ 2ዜና 13:8, 9

መሳፍንት 17:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 8:4, 5
  • +መሳ 21:25

መሳፍንት 17:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 5:2
  • +ዘኁ 3:45፤ ኢያሱ 14:3፤ 18:7

መሳፍንት 17:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 17:1, 5

መሳፍንት 17:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አማካሪና።”

መሳፍንት 17:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጁን ሞላው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 3:10፤ መሳ 17:5

ተዛማጅ ሐሳብ

መሳ. 17:1ኢያሱ 17:14, 15
መሳ. 17:3ዘፀ 20:4፤ ዘሌ 26:1፤ ዘዳ 27:15
መሳ. 17:5ዘፀ 28:6፤ መሳ 8:27
መሳ. 17:5ዘፍ 31:19
መሳ. 17:5ዘኁ 3:10፤ ዘዳ 12:11, 13፤ 2ዜና 13:8, 9
መሳ. 17:61ሳሙ 8:4, 5
መሳ. 17:6መሳ 21:25
መሳ. 17:7ሚክ 5:2
መሳ. 17:7ዘኁ 3:45፤ ኢያሱ 14:3፤ 18:7
መሳ. 17:8መሳ 17:1, 5
መሳ. 17:12ዘኁ 3:10፤ መሳ 17:5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መሳፍንት 17:1-13

መሳፍንት

17 በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ የሚኖር ሚክያስ የተባለ አንድ ሰው ነበር። 2 እሱም እናቱን እንዲህ አላት፦ “1,100 የብር ሰቅል ተወስዶብሽ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼ ነበር፤ ብሩ ያለው እኔ ጋ ነው። የወሰድኩት እኔ ነበርኩ።” በዚህ ጊዜ እናቱ “ልጄ፣ ይሖዋ ይባርክህ” አለችው። 3 በመሆኑም 1,100ውን የብር ሰቅል ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱ ግን “የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት* + እንዲሠራበት ለልጄ ስል ብሩን ከእጄ ለይሖዋ እቀድሰዋለሁ። ለአንተም መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው።

4 እሱም ብሩን ለእናቱ ከመለሰላት በኋላ እናቱ 200 የብር ሰቅል ወስዳ ለብር አንጥረኛው ሰጠችው። እሱም የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት* ሠራበት፤ እነሱም በሚክያስ ቤት ተቀመጡ። 5 ሚክያስ የተባለው ይህ ሰው የአማልክት ቤት ነበረው፤ እሱም ኤፉድና+ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች* + ሠራ፤ ከወንዶች ልጆቹም መካከል አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው።* + 6 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም።+ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።+

7 በዚያ ጊዜ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ የሚኖር ከይሁዳ ቤተሰብ የሆነ አንድ ወጣት ነበር። እሱም ሌዋዊ+ ሲሆን በዚያ ለተወሰነ ጊዜ ተቀምጦ ነበር። 8 ይህም ሰው የሚኖርበት ስፍራ ለመፈለግ በይሁዳ የምትገኘውን የቤተልሔምን ከተማ ለቆ ሄደ። እየተጓዘም ሳለ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ሚክያስ+ ቤት ደረሰ። 9 ከዚያም ሚክያስ “ከየት ነው የመጣኸው?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምኖርበት ስፍራ ለመፈለግ እየሄድኩ ነው” አለው። 10 በመሆኑም ሚክያስ “እንግዲያው እኔ ጋ ተቀመጥ፤ እንደ አባትና*  እንደ ካህንም ሆነህ አገልግለኝ። እኔ ደግሞ በዓመት አሥር የብር ሰቅል እንዲሁም ልብስና ምግብህን እሰጥሃለሁ” አለው። ስለዚህ ሌዋዊው ገባ። 11 በዚህ መንገድ ሌዋዊው ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። 12 በተጨማሪም ሚክያስ ሌዋዊውን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤* + እሱም በሚክያስ ቤት ኖረ። 13 ከዚያም ሚክያስ “ሌዋዊው፣ ካህን ስለሆነልኝ ይሖዋ መልካም እንደሚያደርግልኝ አሁን ተረድቻለሁ” አለ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ