የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ታቦቱ በቂርያትየአሪም (1)

      • ሳሙኤል እስራኤላውያን ‘ይሖዋን ብቻ እንዲያገለግሉ’ አጥብቆ አሳሰበ (2-6)

      • እስራኤላውያን ምጽጳ ላይ ድል ተቀዳጁ (7-14)

      • ሳሙኤል በእስራኤላውያን ላይ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ (15-17)

1 ሳሙኤል 7:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 6:2, 4፤ 1ዜና 13:5, 7

1 ሳሙኤል 7:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወደ ይሖዋ ማልቀስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:28

1 ሳሙኤል 7:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 12:24
  • +ኢያሱ 24:14, 23፤ መሳ 3:7
  • +መሳ 2:13፤ 10:6፤ 1ነገ 11:33
  • +ዘዳ 10:20፤ 13:4፤ ሉቃስ 4:8
  • +ዘዳ 28:1

1 ሳሙኤል 7:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 10:16

1 ሳሙኤል 7:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 20:1፤ 1ሳሙ 10:17፤ 2ነገ 25:23፤ ኤር 40:6
  • +1ሳሙ 12:23፤ ያዕ 5:16

1 ሳሙኤል 7:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 20:3፤ ነህ 9:1፤ ኢዩ 2:12
  • +መሳ 10:10
  • +መሳ 2:18

1 ሳሙኤል 7:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 13:2, 3፤ 1ሳሙ 6:4

1 ሳሙኤል 7:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 12:19፤ ኢሳ 37:4

1 ሳሙኤል 7:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:10
  • +መዝ 99:6

1 ሳሙኤል 7:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:10፤ 2ሳሙ 22:14
  • +ኢያሱ 10:10፤ መሳ 4:15
  • +ዘዳ 20:4፤ 28:7

1 ሳሙኤል 7:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የእርዳታ ድንጋይ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 4:9፤ 24:26
  • +መዝ 44:3

1 ሳሙኤል 7:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 9:16፤ 13:5
  • +1ሳሙ 14:22, 23፤ 17:51

1 ሳሙኤል 7:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:18, 21

1 ሳሙኤል 7:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 3:20፤ 12:11፤ 25:1፤ ሥራ 13:20

1 ሳሙኤል 7:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 16:1
  • +ኢያሱ 15:7, 12፤ 1ሳሙ 11:15
  • +1ሳሙ 7:5

1 ሳሙኤል 7:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 1:1፤ 8:4፤ 19:18
  • +ዘፀ 20:25

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ሳሙ. 7:12ሳሙ 6:2, 4፤ 1ዜና 13:5, 7
1 ሳሙ. 7:2ነህ 9:28
1 ሳሙ. 7:31ሳሙ 12:24
1 ሳሙ. 7:3ኢያሱ 24:14, 23፤ መሳ 3:7
1 ሳሙ. 7:3መሳ 2:13፤ 10:6፤ 1ነገ 11:33
1 ሳሙ. 7:3ዘዳ 10:20፤ 13:4፤ ሉቃስ 4:8
1 ሳሙ. 7:3ዘዳ 28:1
1 ሳሙ. 7:4መሳ 10:16
1 ሳሙ. 7:5መሳ 20:1፤ 1ሳሙ 10:17፤ 2ነገ 25:23፤ ኤር 40:6
1 ሳሙ. 7:51ሳሙ 12:23፤ ያዕ 5:16
1 ሳሙ. 7:62ዜና 20:3፤ ነህ 9:1፤ ኢዩ 2:12
1 ሳሙ. 7:6መሳ 10:10
1 ሳሙ. 7:6መሳ 2:18
1 ሳሙ. 7:7ኢያሱ 13:2, 3፤ 1ሳሙ 6:4
1 ሳሙ. 7:81ሳሙ 12:19፤ ኢሳ 37:4
1 ሳሙ. 7:9ዘሌ 1:10
1 ሳሙ. 7:9መዝ 99:6
1 ሳሙ. 7:101ሳሙ 2:10፤ 2ሳሙ 22:14
1 ሳሙ. 7:10ኢያሱ 10:10፤ መሳ 4:15
1 ሳሙ. 7:10ዘዳ 20:4፤ 28:7
1 ሳሙ. 7:12ኢያሱ 4:9፤ 24:26
1 ሳሙ. 7:12መዝ 44:3
1 ሳሙ. 7:131ሳሙ 9:16፤ 13:5
1 ሳሙ. 7:131ሳሙ 14:22, 23፤ 17:51
1 ሳሙ. 7:14ዘፍ 15:18, 21
1 ሳሙ. 7:151ሳሙ 3:20፤ 12:11፤ 25:1፤ ሥራ 13:20
1 ሳሙ. 7:16ኢያሱ 16:1
1 ሳሙ. 7:16ኢያሱ 15:7, 12፤ 1ሳሙ 11:15
1 ሳሙ. 7:161ሳሙ 7:5
1 ሳሙ. 7:171ሳሙ 1:1፤ 8:4፤ 19:18
1 ሳሙ. 7:17ዘፀ 20:25
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ሳሙኤል 7:1-17

አንደኛ ሳሙኤል

7 በመሆኑም የቂርያትየአሪም ሰዎች መጥተው የይሖዋን ታቦት በኮረብታው ላይ ወደሚገኘው ወደ አቢናዳብ ቤት+ ወሰዱት፤ የይሖዋን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።

2 ታቦቱም ወደ ቂርያትየአሪም ከመጣ ረጅም ጊዜ ይኸውም በአጠቃላይ 20 ዓመት አለፈው፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ይሖዋን መፈለግ* ጀመረ።+ 3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ “በሙሉ ልባችሁ+ ወደ ይሖዋ የምትመለሱ ከሆነ ባዕዳን አማልክትንና+ የአስታሮትን ምስሎች+ ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ልባችሁንም ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ ስጡ፤ እሱን ብቻ አገልግሉ፤+ እሱም ከፍልስጤማውያን እጅ ይታደጋችኋል”+ አላቸው። 4 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን የባአልንና የአስታሮትን ምስሎች አስወግደው ይሖዋን ብቻ አገለገሉ።+

5 ከዚያም ሳሙኤል “እስራኤልን ሁሉ በምጽጳ+ ሰብስቡ፤ እኔም ስለ እናንተ ወደ ይሖዋ እጸልያለሁ”+ አለ። 6 እነሱም በምጽጳ ተሰበሰቡ፤ ከዚያም ውኃ ቀድተው በይሖዋ ፊት አፈሰሱ፤ ያን ዕለትም ሲጾሙ ዋሉ።+ በዚያም “በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል” አሉ።+ ሳሙኤልም በምጽጳ በእስራኤላውያን ላይ ፈራጅ ሆኖ ማገልገል ጀመረ።+

7 ፍልስጤማውያንም እስራኤላውያን በምጽጳ አንድ ላይ መሰብሰባቸውን በሰሙ ጊዜ የፍልስጤም ገዢዎች+ እስራኤልን ለመውጋት ወጡ። እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ፍልስጤማውያንን ፈሩ። 8 ስለሆነም እስራኤላውያን ሳሙኤልን “አምላካችን ይሖዋ እንዲረዳንና ከፍልስጤማውያን እጅ እንዲያድነን ወደ እሱ መጮኽህን አታቁም” አሉት።+ 9 ከዚያም ሳሙኤል አንድ የሚጠባ ግልገል ወስዶ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ+ አድርጎ አቀረበው፤ ሳሙኤልም ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲረዳቸው ተማጸነ፤ ይሖዋም መለሰለት።+ 10 ሳሙኤል የሚቃጠለውን መባ እያቀረበ ሳለ ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት ቀረቡ። ይሖዋም በዚያን ዕለት በፍልስጤማውያን ላይ ኃይለኛ የነጎድጓድ ድምፅ ለቀቀባቸው፤+ ግራ እንዲጋቡም አደረጋቸው፤+ እነሱም በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመቱ።+ 11 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች ከምጽጳ ወጥተው ፍልስጤማውያንን ማሳደዳቸውን ተያያዙት፤ ከቤትካር በስተ ደቡብ እስከሚገኘው አካባቢም ድረስ መቷቸው። 12 ከዚያም ሳሙኤል አንድ ድንጋይ+ ወስዶ በምጽጳ እና በየሻና መካከል አስቀመጠው፤ ስሙንም ኤቤንዔዘር* አለው፤ ይህን ያለው “ይሖዋ እስካሁን ድረስ ረድቶናል”+ ሲል ነው። 13 በዚህ ሁኔታ ፍልስጤማውያን ድል ተመቱ፤ ዳግመኛም ወደ እስራኤላውያን ክልል መጥተው አያውቁም፤+ በሳሙኤል ዘመን ሁሉ የይሖዋ እጅ በፍልስጤማውያን ላይ ነበር።+ 14 በተጨማሪም ፍልስጤማውያን ከእስራኤላውያን ላይ የወሰዷቸው ከኤቅሮን እስከ ጌት ያሉት ከተሞች ለእስራኤላውያን ተመለሱላቸው፤ እንዲሁም እስራኤላውያን በእነዚህ ከተሞች ሥር ያሉትን ክልሎች ከፍልስጤማውያን እጅ አስለቀቁ።

በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከልም ሰላም ወረደ።+

15 ሳሙኤልም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ።+ 16 በየዓመቱም በቤቴል፣+ በጊልጋል+ እና በምጽጳ+ በመዘዋወር በእነዚህ አካባቢዎች ሁሉ ለሚገኙ እስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። 17 ሆኖም ቤቱ የሚገኘው በራማ+ ስለነበር ወደዚያ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ለእስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ