የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ጢሞቴዎስ 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ጢሞቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ወጣቶችንና አረጋውያንን በአግባቡ መያዝ (1, 2)

      • ለመበለቶች የሚሰጥ ድጋፍ (3-16)

        • ለቤተሰብ አባላት የሚያስፈልገውን ማቅረብ (8)

      • ተግተው የሚሠሩ ሽማግሌዎችን ማክበር (17-25)

        • ‘ለሆድህ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ’ (23)

1 ጢሞቴዎስ 5:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:32

1 ጢሞቴዎስ 5:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በእርግጥ ለተቸገሩ መበለቶች።” ረዳት የሌላቸውን መበለቶች ያመለክታል።

  • *

    ቃል በቃል “አክብሮት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 5:16

1 ጢሞቴዎስ 5:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 5:8
  • +ማቴ 15:4፤ ኤፌ 6:2
  • +ያዕ 1:27

1 ጢሞቴዎስ 5:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:34
  • +ሉቃስ 2:36, 37

1 ጢሞቴዎስ 5:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትእዛዛት።”

1 ጢሞቴዎስ 5:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 15:4-6

1 ጢሞቴዎስ 5:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 2:15
  • +ዕብ 13:2፤ 1ጴጥ 4:9
  • +ዮሐ 13:5, 14
  • +1ጢሞ 5:16፤ ያዕ 1:27
  • +ሥራ 9:39

1 ጢሞቴዎስ 5:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በፊት የገቡትን ቃል።”

1 ጢሞቴዎስ 5:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ተሰ 3:11

1 ጢሞቴዎስ 5:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:8, 9
  • +1ጢሞ 2:15

1 ጢሞቴዎስ 5:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በእርግጥ የተቸገሩ መበለቶችን።” ረዳት የሌላቸውን መበለቶች ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:11፤ 1ጢሞ 5:5፤ ያዕ 1:27

1 ጢሞቴዎስ 5:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 5:2, 3
  • +1ተሰ 5:12፤ ዕብ 13:7
  • +ሥራ 28:10፤ ዕብ 13:17

1 ጢሞቴዎስ 5:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 25:4፤ 1ቆሮ 9:7, 9
  • +ዘሌ 19:13፤ ማቴ 10:9, 10፤ ሉቃስ 10:7፤ ገላ 6:6

1 ጢሞቴዎስ 5:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 19:15፤ ማቴ 18:16

1 ጢሞቴዎስ 5:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሌሎቹ እንዲፈሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 15:34፤ 1ዮሐ 3:9
  • +ቲቶ 1:7, 9, 13፤ ራእይ 3:19

1 ጢሞቴዎስ 5:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:15፤ ያዕ 3:17

1 ጢሞቴዎስ 5:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ማንኛውንም ሰው ለመሾም አትቸኩል ማለት ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 6:5, 6፤ 14:23፤ 1ጢሞ 3:2, 6፤ 4:14

1 ጢሞቴዎስ 5:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ውኃ ብቻ አትጠጣ።”

1 ጢሞቴዎስ 5:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 7:11፤ ዕብ 4:13

1 ጢሞቴዎስ 5:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:16
  • +1ቆሮ 4:5

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ጢሞ. 5:1ዘሌ 19:32
1 ጢሞ. 5:31ጢሞ 5:16
1 ጢሞ. 5:41ጢሞ 5:8
1 ጢሞ. 5:4ማቴ 15:4፤ ኤፌ 6:2
1 ጢሞ. 5:4ያዕ 1:27
1 ጢሞ. 5:51ቆሮ 7:34
1 ጢሞ. 5:5ሉቃስ 2:36, 37
1 ጢሞ. 5:8ማቴ 15:4-6
1 ጢሞ. 5:10ሥራ 9:39
1 ጢሞ. 5:101ጢሞ 2:15
1 ጢሞ. 5:10ዕብ 13:2፤ 1ጴጥ 4:9
1 ጢሞ. 5:10ዮሐ 13:5, 14
1 ጢሞ. 5:101ጢሞ 5:16፤ ያዕ 1:27
1 ጢሞ. 5:132ተሰ 3:11
1 ጢሞ. 5:141ቆሮ 7:8, 9
1 ጢሞ. 5:141ጢሞ 2:15
1 ጢሞ. 5:16ዘዳ 15:11፤ 1ጢሞ 5:5፤ ያዕ 1:27
1 ጢሞ. 5:171ጴጥ 5:2, 3
1 ጢሞ. 5:171ተሰ 5:12፤ ዕብ 13:7
1 ጢሞ. 5:17ሥራ 28:10፤ ዕብ 13:17
1 ጢሞ. 5:18ዘዳ 25:4፤ 1ቆሮ 9:7, 9
1 ጢሞ. 5:18ዘሌ 19:13፤ ማቴ 10:9, 10፤ ሉቃስ 10:7፤ ገላ 6:6
1 ጢሞ. 5:19ዘዳ 19:15፤ ማቴ 18:16
1 ጢሞ. 5:201ቆሮ 15:34፤ 1ዮሐ 3:9
1 ጢሞ. 5:20ቲቶ 1:7, 9, 13፤ ራእይ 3:19
1 ጢሞ. 5:21ዘሌ 19:15፤ ያዕ 3:17
1 ጢሞ. 5:22ሥራ 6:5, 6፤ 14:23፤ 1ጢሞ 3:2, 6፤ 4:14
1 ጢሞ. 5:24ኢያሱ 7:11፤ ዕብ 4:13
1 ጢሞ. 5:25ማቴ 5:16
1 ጢሞ. 5:251ቆሮ 4:5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ጢሞቴዎስ 5:1-25

ለጢሞቴዎስ የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

5 ሽማግሌ የሆነውን በኃይለ ቃል አትናገረው።+ ከዚህ ይልቅ እንደ አባት ቆጥረህ በደግነት ምከረው፤ ወጣት ወንዶችን እንደ ወንድሞች፣ 2 አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እንደ እህቶች አድርገህ በፍጹም ንጽሕና ያዛቸው።

3 በእርግጥ መበለት ለሆኑ መበለቶች*+ አሳቢነት* አሳያቸው። 4 ሆኖም አንዲት መበለት ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ካሏት እነዚህ ልጆች በመጀመሪያ በራሳቸው ቤተሰብ+ ውስጥ ለአምላክ የማደርን ባሕርይ ማንጸባረቅን እንዲሁም ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው የሚገባቸውን ብድራት መክፈልን ይማሩ፤+ ይህ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ነውና።+ 5 በእርግጥ መበለት የሆነችና ምንም የሌላት ሴት ተስፋዋን በአምላክ ላይ ትጥላለች+ እንዲሁም ሌት ተቀን ያለማሰለስ ምልጃና ጸሎት ታቀርባለች።+ 6 ለሥጋዊ ፍላጎቷ ያደረች መበለት ግን በሕይወት ብትኖርም የሞተች ናት። 7 ስለዚህ ከነቀፋ ነፃ መሆን ይችሉ ዘንድ እነዚህን መመሪያዎች* መስጠትህን ቀጥል። 8 በእርግጥም አንድ ሰው የራሱ ለሆኑት በተለይ ደግሞ ለቤተሰቡ አባላት የሚያስፈልጋቸውን ነገር የማያቀርብ ከሆነ እምነትን የካደ ከመሆኑም በላይ እምነት የለሽ ከሆነ ሰው የከፋ ነው።+

9 አንዲት መበለት ከ60 ዓመት በላይ ከሆነች በመዝገብ ላይ ትጻፍ፤ ደግሞም የአንድ ባል ሚስት የነበረች ልትሆን ይገባል፤ 10 እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፣+ እንግዶችን በመቀበል፣+ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣+ የተቸገሩትን በመርዳትና+ ማንኛውንም በጎ ተግባር በትጋት በማከናወን በመልካም ሥራ ጥሩ ስም ያተረፈች+ ልትሆን ይገባል።

11 በዕድሜ ያልገፉ መበለቶች ግን መዝገብ ላይ መጻፍ የለባቸውም፤ የፆታ ፍላጎታቸው በክርስቲያናዊ አገልግሎታቸው ላይ እንቅፋት በሚፈጥርበት ጊዜ ማግባት ይፈልጋሉና። 12 ደግሞም የመጀመሪያውን የእምነት ቃላቸውን* ስላፈረሱ በራሳቸው ላይ ፍርድ ያመጣሉ። 13 ከዚህ በተጨማሪ በየቤቱ እየዞሩ ሥራ ፈት ይሆናሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን ማውራት ስለማይገባቸው ነገሮች እያወሩ ሐሜተኞችና በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።+ 14 ስለዚህ በዕድሜ ያልገፉ መበለቶች እንዲያገቡ፣+ ልጆች እንዲወልዱ፣+ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩና ተቃዋሚው ትችት ሊሰነዝር የሚችልበት አጋጣሚ እንዲያገኝ ከማድረግ እንዲቆጠቡ እፈልጋለሁ። 15 እንዲያውም አንዳንዶቹ ከዚህ በፊት ሰይጣንን ለመከተል ዞር ብለዋል። 16 አንዲት አማኝ የሆነች ሴት፣ መበለት የሆኑ ዘመዶች ቢኖሯት ጉባኤው ሸክም እንዳይበዛበት እሷ ትርዳቸው። በዚህ መንገድ ጉባኤው በእርግጥ መበለት የሆኑትን* መርዳት ይችላል።+

17 በመልካም ሁኔታ የሚያስተዳድሩ+ በተለይ ደግሞ በመናገርና በማስተማር ተግተው የሚሠሩ+ ሽማግሌዎች እጥፍ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል።+ 18 የቅዱስ መጽሐፉ ቃል “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር”፤+ እንዲሁም “ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋል” ይላልና።+ 19 በሁለት ወይም በሦስት ምሥክሮች+ ማስረጃ ካልሆነ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብን ክስ አትቀበል። 20 ለሌሎቹ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን* ኃጢአት የመሥራት ልማድ ያላቸውን ሰዎች+ በሁሉ ፊት ውቀሳቸው።+ 21 እነዚህን መመሪያዎች መሠረተ ቢስ ከሆነ ጥላቻና ከአድልዎ በራቀ መንገድ እንድትጠብቅ በአምላክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስና በተመረጡት መላእክት ፊት በጥብቅ አዝሃለሁ።+

22 በማንም ሰው ላይ እጅህን ለመጫን አትቸኩል፤*+ እንዲሁም በሌሎች ኃጢአት ተካፋይ አትሁን፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ።

23 ከእንግዲህ ውኃ አትጠጣ፤* ከዚህ ይልቅ ለሆድህና በተደጋጋሚ ለሚነሳብህ ሕመም ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ።

24 የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በይፋ የታወቀ ስለሚሆን ወዲያውኑ ፍርድ ያስከትላል፤ የሌሎቹ ሰዎች ኃጢአት ደግሞ ውሎ አድሮ መታወቁ አይቀርም።+ 25 በተመሳሳይም መልካም ሥራዎች በይፋ የታወቁ ናቸው፤+ በይፋ ያልታወቁትም ቢሆኑ ተደብቀው ሊቀሩ አይችሉም።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ