የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ጳስኮር ኤርምያስን መታው (1-6)

      • ኤርምያስ መስበኩን ሊያቆም አልቻለም (7-13)

        • የአምላክ ቃል እንደሚነድ እሳት ነው (9)

        • ይሖዋ እንደ አስፈሪ ተዋጊ ነው (11)

      • ኤርምያስ ያሰማው እሮሮ (14-18)

ኤርምያስ 20:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 16:10

ኤርምያስ 20:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ዙሪያ ገባው ሽብር” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 6:25

ኤርምያስ 20:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:32
  • +ኤር 25:9፤ 39:9

ኤርምያስ 20:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 20:17፤ 24:11, 13፤ 25:13-15፤ ሰቆ 1:10
  • +2ዜና 36:10፤ ኤር 15:13

ኤርምያስ 20:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 14:14፤ 28:15፤ 29:21

ኤርምያስ 20:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 3:14፤ ሚክ 3:8
  • +መዝ 22:7፤ ኤር 15:10, 15

ኤርምያስ 20:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:16፤ ኤር 6:10

ኤርምያስ 20:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 19:2, 4፤ ዮናስ 1:3
  • +ኤር 6:11፤ አሞጽ 3:8፤ ሥራ 4:19, 20

ኤርምያስ 20:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 31:13
  • +መዝ 38:16

ኤርምያስ 20:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:8፤ ሮም 8:31
  • +መዝ 27:2፤ ኤር 15:15, 20፤ 17:18
  • +መዝ 6:10

ኤርምያስ 20:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጥልቅ ስሜትንና።” ቃል በቃል “ኩላሊትንና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 17:10
  • +መዝ 59:10፤ ኤር 17:18
  • +ኤር 11:20፤ 1ጴጥ 2:23

ኤርምያስ 20:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የድሃውን ነፍስ።”

ኤርምያስ 20:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 3:3፤ ኤር 15:10

ኤርምያስ 20:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 10:18

ኤርምያስ 20:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 3:20

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 20:22ዜና 16:10
ኤር. 20:3ኤር 6:25
ኤር. 20:4ዘዳ 28:32
ኤር. 20:4ኤር 25:9፤ 39:9
ኤር. 20:52ነገ 20:17፤ 24:11, 13፤ 25:13-15፤ ሰቆ 1:10
ኤር. 20:52ዜና 36:10፤ ኤር 15:13
ኤር. 20:6ኤር 14:14፤ 28:15፤ 29:21
ኤር. 20:7ሕዝ 3:14፤ ሚክ 3:8
ኤር. 20:7መዝ 22:7፤ ኤር 15:10, 15
ኤር. 20:82ዜና 36:16፤ ኤር 6:10
ኤር. 20:91ነገ 19:2, 4፤ ዮናስ 1:3
ኤር. 20:9ኤር 6:11፤ አሞጽ 3:8፤ ሥራ 4:19, 20
ኤር. 20:10መዝ 31:13
ኤር. 20:10መዝ 38:16
ኤር. 20:11ኤር 1:8፤ ሮም 8:31
ኤር. 20:11መዝ 27:2፤ ኤር 15:15, 20፤ 17:18
ኤር. 20:11መዝ 6:10
ኤር. 20:12ኤር 17:10
ኤር. 20:12መዝ 59:10፤ ኤር 17:18
ኤር. 20:12ኤር 11:20፤ 1ጴጥ 2:23
ኤር. 20:14ኢዮብ 3:3፤ ኤር 15:10
ኤር. 20:17ኢዮብ 10:18
ኤር. 20:18ኢዮብ 3:20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 20:1-18

ኤርምያስ

20 በይሖዋ ቤት ዋና ሹም የነበረው የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር፣ ኤርምያስ እነዚህን ነገሮች ሲተነብይ ሰማ። 2 ጳስኮርም ነቢዩ ኤርምያስን መታው፤ ከዚያም በይሖዋ ቤት ባለው በላይኛው የቢንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።+ 3 ይሁንና በማግስቱ ጳስኮር ኤርምያስን ከእግር ግንዱ ውስጥ ፈታው፤ በዚህ ጊዜ ኤርምያስ እንዲህ አለው፦

“ይሖዋ፣ ማጎርሚሳቢብ*+ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም። 4 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንተም ሆንክ ወዳጆችህ እንድትሸበሩ አደርጋለሁ፤ እነሱም ዓይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤+ ይሁዳንም ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እሱም በግዞት ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።+ 5 የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን ሁሉ፣ ውድ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ እንዲሁም የይሁዳን ነገሥታት ውድ ሀብት ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።+ እነሱም ይበዘብዟቸዋል፤ ወደ ባቢሎንም ያግዟቸዋል።+ 6 ጳስኮር ሆይ፣ አንተና በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ በግዞት ትወሰዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤ በዚያም ትሞታለህ፤ ከወዳጆችህም ሁሉ ጋር በዚያ ትቀበራለህ፤ ምክንያቱም ለእነሱ የሐሰት ትንቢት ተናግረሃል።’”+

 7 ይሖዋ ሆይ፣ አሞኘኸኝ፤ እኔም ተሞኘሁ።

አንተ በእኔ ላይ በረታህ፤ አሸነፍክም።+

እኔም ቀኑን ሙሉ መሳለቂያ ሆንኩ፤

ሁሉም ያፌዙብኛል።+

 8 በተናገርኩ ቁጥር እጮኻለሁና፤

“ዓመፅና ጥፋት!” ብዬ አውጃለሁ።

የይሖዋ ቃል ቀኑን ሙሉ ስድብና ፌዝ አስከትሎብኛል።+

 9 ስለዚህ “እሱን አላነሳም፤

ከእንግዲህም በስሙ አልናገርም” አልኩ።+

ይሁንና ቃሉ በልቤ ውስጥ እንዳለ፣ በአጥንቶቼም ውስጥ እንደገባ የሚነድ እሳት ሆነብኝ፤

አፍኜ መያዝ አቃተኝ፤

ከዚህ በላይ መቋቋም አልቻልኩም።+

10 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁና፤

በዙሪያዬ ያለው ሁኔታ አሸብሮኛል።+

“አውግዙት፤ እናውግዘው!”

ሰላም የሚመኝልኝ ሰው ሁሉ የእኔን ውድቀት ይጠባበቃል፦+

“ምናልባት ይታለል ይሆናል፤

እኛም እናሸንፈዋለን፤ ደግሞም እንበቀለዋለን።”

11 ይሖዋ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነበር።+

ከዚህም የተነሳ የሚያሳድዱኝ ሰዎች ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም።+

ስለማይሳካላቸውም ለከፍተኛ ኀፍረት ይዳረጋሉ።

የሚደርስባቸው ዘላለማዊ ውርደት ፈጽሞ አይረሳም።+

12 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ጻድቁን ትመረምራለህ፤

የውስጥ ሐሳብንና* ልብን ታያለህ።+

በእነሱ ላይ የምትወስደውን የበቀል እርምጃ እንዳይ አድርገኝ፤+

ጉዳዬን ለአንተ አቅርቤአለሁና።+

13 ለይሖዋ ዘምሩ! ይሖዋን አወድሱ!

እሱ ድሃውን* ከክፉ አድራጊዎች እጅ ታድጓልና።

14 የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን!

እናቴ እኔን የወለደችበት ቀን አይባረክ!+

15 ለአባቴ “ልጅ፣ አዎ ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል!”

የሚል ምሥራች አብስሮ እጅግ ደስ ያሰኘው

ሰው የተረገመ ይሁን።

16 ያ ሰው፣ ይሖዋ ያላንዳች ጸጸት እንደገለበጣቸው ከተሞች ይሁን።

በማለዳ ዋይታ፣ በቀትርም የጦርነት ሁካታ ይስማ።

17 እናቴ የመቃብሬ ቦታ እንድትሆን፣

ማህፀኗም ዘወትር እርጉዝ እንደሆነ ይኖር ዘንድ፣

ገና በማህፀን ሳለሁ ለምን አልገደለኝም?+

18 ችግርንና ሐዘንን እንዳይ፣

ዕድሜዬም በኀፍረት እንዲያከትም

ለምን ከማህፀን ወጣሁ?+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ