የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኤርምያስ ገንቦውን እንዲሰብር ተነገረው (1-15)

        • ልጆቻቸውን ለባአል ሠዉ (5)

ኤርምያስ 19:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 18:2

ኤርምያስ 19:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:8, 12፤ 2ዜና 28:1, 3፤ ኤር 7:31

ኤርምያስ 19:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 22:16, 17፤ ኢሳ 65:11
  • +2ዜና 33:1, 4
  • +2ነገ 21:16፤ ኢሳ 59:7፤ ኤር 2:34፤ ሰቆ 4:13፤ ማቴ 23:34, 35

ኤርምያስ 19:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈጽሞ ወደ አእምሮዬ መጥቶ የማያውቀውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:21፤ 2ዜና 28:1, 3፤ 33:1, 6፤ ኢሳ 57:5፤ ኤር 7:31፤ 32:35

ኤርምያስ 19:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:32

ኤርምያስ 19:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውንም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:25, 26፤ መዝ 79:2፤ ኤር 7:33፤ 16:4

ኤርምያስ 19:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 9:8፤ ኤር 18:16፤ ሰቆ 2:15

ኤርምያስ 19:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳቸውን የሚሹ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:29፤ ዘዳ 28:53፤ ሰቆ 2:20፤ 4:10፤ ሕዝ 5:10

ኤርምያስ 19:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:32

ኤርምያስ 19:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 8:1, 2፤ ሶፎ 1:4, 5
  • +ኤር 7:18፤ 32:29
  • +መዝ 79:1

ኤርምያስ 19:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቃሌን ላለመታዘዝ አንገታቸውን አደንድነዋል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:17, 29፤ ዘካ 7:12

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 19:1ኤር 18:2
ኤር. 19:2ኢያሱ 15:8, 12፤ 2ዜና 28:1, 3፤ ኤር 7:31
ኤር. 19:42ነገ 22:16, 17፤ ኢሳ 65:11
ኤር. 19:42ዜና 33:1, 4
ኤር. 19:42ነገ 21:16፤ ኢሳ 59:7፤ ኤር 2:34፤ ሰቆ 4:13፤ ማቴ 23:34, 35
ኤር. 19:5ዘሌ 18:21፤ 2ዜና 28:1, 3፤ 33:1, 6፤ ኢሳ 57:5፤ ኤር 7:31፤ 32:35
ኤር. 19:6ኤር 7:32
ኤር. 19:7ዘዳ 28:25, 26፤ መዝ 79:2፤ ኤር 7:33፤ 16:4
ኤር. 19:81ነገ 9:8፤ ኤር 18:16፤ ሰቆ 2:15
ኤር. 19:9ዘሌ 26:29፤ ዘዳ 28:53፤ ሰቆ 2:20፤ 4:10፤ ሕዝ 5:10
ኤር. 19:11ኤር 7:32
ኤር. 19:13ኤር 8:1, 2፤ ሶፎ 1:4, 5
ኤር. 19:13ኤር 7:18፤ 32:29
ኤር. 19:13መዝ 79:1
ኤር. 19:15ነህ 9:17, 29፤ ዘካ 7:12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 19:1-15

ኤርምያስ

19 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ሄደህ፣ ከሸክላ ሠሪ ገንቦ ግዛ።+ ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከካህናቱ ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ይዘህ 2 በገል በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሂኖም ልጅ ሸለቆ+ ውጣ። የምነግርህንም ቃል በዚያ አውጅ። 3 እንዲህ ትላለህ፦ ‘እናንተ የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“‘“በዚህ ስፍራ ላይ ጥፋት ላመጣ ነው፤ ስለሚመጣው ጥፋት የሚሰማ ሰው ሁሉ ጆሮውን ይነዝረዋል። 4 ምክንያቱም እኔን ትተውኛል፤+ ይህን ስፍራም የማይታወቅ ቦታ አድርገውታል።+ በዚህ ስፍራ እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እንዲሁም የይሁዳ ነገሥታት ለማያውቋቸው ሌሎች አማልክት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ይህን ስፍራም በንጹሐን ደም ሞልተውታል።+ 5 እኔ ያላዘዝኩትን ወይም ያልተናገርኩትን፣ በልቤም እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶች ልጆቻቸውን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ለባአል በእሳት ለማቃጠል ከፍ ያሉትን የባአል የማምለኪያ ቦታዎች ሠሩ።”’+

6 “‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ስለዚህ፣ እነሆ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል።+ 7 በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ዕቅድ አጨናግፋለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት በሰይፍ እንዲወድቁ፣ ሕይወታቸውንም* በሚሹ ሰዎች እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ። አስከሬናቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል እንዲሆን እሰጣለሁ።+ 8 ይህችንም ከተማ አስፈሪ ቦታና ማፏጫ አደርጋታለሁ። በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በደረሰባት መቅሰፍት የተነሳ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ደግሞም ያፏጫል።+ 9 ጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ* ሰዎች ሲከቧቸውና መፈናፈኛ አሳጥተው ሲያስጨንቋቸው የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸው የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።”’+

10 “ከዚያም ገንቦውን ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ስበረው፤ 11 እንዲህም በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ ሰው የሸክላ ሠሪን ዕቃ ሊጠገን በማይችል መንገድ እንደሚሰብረው፣ እኔም ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰባብራለሁ፤ እነሱም የመቃብር ቦታ እስኪታጣ ድረስ የሞቱትን በቶፌት ይቀብራሉ።”’+

12 “‘ይህችን ከተማ እንደ ቶፌት አደርጋት ዘንድ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎቹ ላይ ይህን እፈጽማለሁ’ ይላል ይሖዋ። 13 ‘የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ አዎ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለሰማያት ሠራዊት መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውና+ ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባዎች ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ+ እንደዚህ ስፍራ፣ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።’”+

14 ኤርምያስ፣ ይሖዋ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ሲመለስ በይሖዋ ቤት ግቢ ቆሞ ለመላው ሕዝብ እንዲህ አለ፦ 15 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ሁሉ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቃሌን ለመታዘዝ በግትርነት አሻፈረን ብለዋል።’”*+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ