የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ሰው ኃጢአት ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ (1-13)

        • የመጀመሪያው ውሸት (4, 5)

      • ይሖዋ በዓመፀኞቹ ላይ ያስተላለፈው ፍርድ (14-24)

        • ስለ ሴቲቱ ዘር የተነገረ ትንቢት (15)

        • ከኤደን ገነት ተባረሩ (23, 24)

ዘፍጥረት 3:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በጣም መሠሪ፤ እጅግ ተንኮለኛ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 11:3፤ ራእይ 12:9፤ 20:2
  • +ዘፍ 2:17

ዘፍጥረት 3:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:16

ዘፍጥረት 3:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:8, 9

ዘፍጥረት 3:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 8:44፤ 1ዮሐ 3:8

ዘፍጥረት 3:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:22

ዘፍጥረት 3:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 11:3፤ 1ጢሞ 2:14፤ ያዕ 1:14, 15
  • +ሮም 5:12

ዘፍጥረት 3:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:21

ዘፍጥረት 3:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:25
  • +ዘፍ 2:17

ዘፍጥረት 3:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 11:3፤ 1ጢሞ 2:14

ዘፍጥረት 3:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:1

ዘፍጥረት 3:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ያቆስላል፤ ይመታል።”

  • *

    ወይም “ትመታለህ፤ ትጨፈልቃለህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 12:9
  • +ራእይ 12:1
  • +ዮሐ 8:44፤ 1ዮሐ 3:10
  • +ዘፍ 22:18፤ 49:10፤ ገላ 3:16, 29
  • +ራእይ 12:7, 17
  • +ራእይ 20:2, 10
  • +ማቴ 27:50፤ ሥራ 3:15

ዘፍጥረት 3:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ምድራዊ ሰው፤ ሰው፤ የሰው ዘር” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:17
  • +ዘፍ 5:29
  • +ሮም 8:20

ዘፍጥረት 3:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:7
  • +መዝ 104:29፤ መክ 3:20፤ 12:7

ዘፍጥረት 3:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ሕያው” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:26

ዘፍጥረት 3:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:7

ዘፍጥረት 3:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:5
  • +ዘፍ 2:9

ዘፍጥረት 3:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:19
  • +ዘፍ 2:8

ዘፍጥረት 3:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 80:1፤ ኢሳ 37:16፤ ሕዝ 10:4

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 3:12ቆሮ 11:3፤ ራእይ 12:9፤ 20:2
ዘፍ. 3:1ዘፍ 2:17
ዘፍ. 3:2ዘፍ 2:16
ዘፍ. 3:3ዘፍ 2:8, 9
ዘፍ. 3:4ዮሐ 8:44፤ 1ዮሐ 3:8
ዘፍ. 3:5ዘፍ 3:22
ዘፍ. 3:62ቆሮ 11:3፤ 1ጢሞ 2:14፤ ያዕ 1:14, 15
ዘፍ. 3:6ሮም 5:12
ዘፍ. 3:7ዘፍ 3:21
ዘፍ. 3:11ዘፍ 2:25
ዘፍ. 3:11ዘፍ 2:17
ዘፍ. 3:132ቆሮ 11:3፤ 1ጢሞ 2:14
ዘፍ. 3:14ዘፍ 3:1
ዘፍ. 3:15ራእይ 12:9
ዘፍ. 3:15ራእይ 12:1
ዘፍ. 3:15ዮሐ 8:44፤ 1ዮሐ 3:10
ዘፍ. 3:15ዘፍ 22:18፤ 49:10፤ ገላ 3:16, 29
ዘፍ. 3:15ራእይ 12:7, 17
ዘፍ. 3:15ራእይ 20:2, 10
ዘፍ. 3:15ማቴ 27:50፤ ሥራ 3:15
ዘፍ. 3:17ዘፍ 2:17
ዘፍ. 3:17ዘፍ 5:29
ዘፍ. 3:17ሮም 8:20
ዘፍ. 3:19ዘፍ 2:7
ዘፍ. 3:19መዝ 104:29፤ መክ 3:20፤ 12:7
ዘፍ. 3:20ሥራ 17:26
ዘፍ. 3:21ዘፍ 3:7
ዘፍ. 3:22ዘፍ 3:5
ዘፍ. 3:22ዘፍ 2:9
ዘፍ. 3:23ዘፍ 3:19
ዘፍ. 3:23ዘፍ 2:8
ዘፍ. 3:24መዝ 80:1፤ ኢሳ 37:16፤ ሕዝ 10:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 3:1-24

ዘፍጥረት

3 እባብም+ ይሖዋ አምላክ ከሠራቸው የዱር እንስሳት ሁሉ እጅግ ጠንቃቃ* ነበር። በመሆኑም ሴቲቱን “በእርግጥ አምላክ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም ዛፍ አትብሉ’ ብሏችኋል?”+ ሲል ጠየቃት። 2 በዚህ ጊዜ ሴቲቱ እባቡን እንዲህ አለችው፦ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት ዛፎች ፍሬ መብላት እንችላለን።+ 3 ይሁንና በአትክልቱ ስፍራ መካከል የሚገኘውን ዛፍ+ ፍሬ በተመለከተ አምላክ ‘ከእሱ አትብሉ፤ ፈጽሞም አትንኩት፤ አለዚያ ትሞታላችሁ’ ብሏል።” 4 በዚህ ጊዜ እባቡ ሴቲቱን እንዲህ አላት፦ “መሞት እንኳ ፈጽሞ አትሞቱም።+ 5 አምላክ ከዛፉ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንደሚገለጡና መልካምና ክፉን በማወቅ ረገድ እንደ አምላክ እንደምትሆኑ+ ስለሚያውቅ ነው።”

6 በዚህም የተነሳ ሴቲቱ ዛፉ ለመብል መልካም፣ ሲያዩትም የሚያጓጓ እንደሆነ ተመለከተች፤ ዛፉ ለዓይን የሚማርክ ነበር። ስለሆነም ከዛፉ ፍሬ ወስዳ በላች።+ ባሏም አብሯት ሲሆን ለእሱም ሰጠችው፤ እሱም በላ።+ 7 ከዚያም የሁለቱም ዓይኖች ተገለጡ፤ ራቁታቸውን መሆናቸውንም አስተዋሉ። በመሆኑም የበለስ ቅጠል በመስፋት የሚያሸርጡት ነገር ለራሳቸው ሠሩ።+

8 በኋላም ሰውየውና ሚስቱ ቀኑ ነፋሻማ በሆነበት ጊዜ ላይ ይሖዋ አምላክ በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ሲሄድ ድምፁን ሰሙ፤ እነሱም በአትክልቱ ስፍራ ባሉት ዛፎች መካከል በመግባት ከይሖዋ አምላክ ፊት ተደበቁ። 9 ይሖዋ አምላክም ሰውየውን በተደጋጋሚ በመጣራት “የት ነህ?” አለው። 10 በመጨረሻም ሰውየው “በአትክልቱ ስፍራ ድምፅህን ሰማሁ፤ ሆኖም ራቁቴን ስለነበርኩ ፈራሁ፤ ስለሆነም ተደበቅኩ” አለ። 11 እሱም “ራቁትህን+ እንደሆንክ ማን ነገረህ? እንዳትበላ ብዬ ካዘዝኩህ ዛፍ+ በላህ?” አለው። 12 ሰውየውም “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ይህች ሴት ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። 13 ከዚያም ይሖዋ አምላክ ሴቲቱን “ለመሆኑ ይህ ያደረግሽው ነገር ምንድን ነው?” አላት። ሴቲቱም “እባቡ አታለለኝና በላሁ”+ ስትል መለሰች።

14 ከዚያም ይሖዋ አምላክ እባቡን+ እንዲህ አለው፦ “ይህን ስላደረግክ ከቤት እንስሳት ሁሉ እንዲሁም ከዱር እንስሳት ሁሉ የተረገምክ ትሆናለህ። በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በሆድህ እየተሳብክ ትሄዳለህ፤ እንዲሁም አፈር ትበላለህ። 15 በአንተና+ በሴቲቱ+ መካከል እንዲሁም በዘርህና+ በዘሯ+ መካከል ጠላትነት+ እንዲኖር አደርጋለሁ፤ እሱ ራስህን ይጨፈልቃል፤*+ አንተም ተረከዙን ታቆስላለህ።”*+

16 ሴቲቱንም እንዲህ አላት፦ “በእርግዝናሽ ወቅት የሚሰማሽን ሕመም በእጅጉ አበዛለሁ፤ ልጆች የምትወልጂውም በሥቃይ ይሆናል፤ ምኞትሽ ሁሉ ባልሽ ይሆናል፤ እሱ ደግሞ ይገዛሻል።”

17 አዳምንም* እንዲህ አለው፦ “የሚስትህን ቃል ስለሰማህና ‘ከእሱ አትብላ’ ብዬ ካዘዝኩህ ዛፍ+ ወስደህ ስለበላህ በአንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን።+ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የምድርን ፍሬ በሥቃይ ትበላለህ።+ 18 ምድርም እሾህና አሜኬላ ታበቅልብሃለች፤ አንተም በሜዳ ላይ የሚበቅለውን ተክል ትበላለህ። 19 ከመሬት ስለተገኘህ+ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።”+

20 ከዚህ በኋላ አዳም ሚስቱን ሔዋን* ብሎ ጠራት፤ ምክንያቱም እሷ የሕያዋን ሁሉ እናት ትሆናለች።+ 21 ይሖዋ አምላክም ረጅም ልብስ ከቆዳ ሠርቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።+ 22 ከዚያም ይሖዋ አምላክ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ሰውየው መልካምና ክፉን በማወቅ ረገድ ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል።+ አሁን ደግሞ እጁን በመዘርጋት ከሕይወት ዛፍ+ ፍሬ ወስዶ እንዳይበላና ለዘላለም እንዳይኖር . . .” 23 ይህን ካለ በኋላም የተገኘበትን መሬት እንዲያርስ፣+ ይሖዋ አምላክ አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ+ አባረረው። 24 ሰውየውንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና+ ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ